የብርሃንና ሰላም ህትመት ቴክኖሎጂ ኮሌጅ

ይምጡና ኮሌጃችን ባዘጋጀው የተለያዩ የህትመት ስልጠና ዓይነቶች ሰልጥነው በህትመቱ ዘርፍ ጊዜው የሚፈልገውን በቂ እውቀትና ክህሎት ያግኙ

ዘመኑ የደረሰበትን ዲጅታል የህትመት ቴክኖሎጂ በመጠቀም፤ በህትመት ቴክኖሎጂ ብቃት ያለው ባለሙያን በማፍራት እና አሰራርን ቀልጣፋ በማድረግ ተመራጭ የህትመት አገልግሎት መስጠትና አትራፊ ሆኖ በመቀጠል ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅኦ ማድረግ
በ2022 በምሥራቅ አፍሪካ ተወዳዳሪ የሆነ የህትመት ተቋም ሆኖ ማየት፡፡
 በደንበኞች ፍላጎት መሰረት ልዩ ልዩ ህትመቶችን በጥራትና በጊዜ ሰርቶ ማስረከብ፤  መልካም የሥራ ግንኙነት መፍጠርና ለደንበኞች ክብር መስጠት፤  በህትመት ሙያ ልምድ ያካበተ ሠራተኛ መኖር፤  ተባብሮ የመስራት ልምድን ማዳበር፤  በደንበኞች ታማኝነትና ተቀባይነትን ማግኘት፤  የድርጅቱን መልካም ስም ማስጠበቅ

የሕትመት አገልግሎቶች

ድርጅቱ ከሚሰጣቸው የሕትመት አገልግሎቶች አንፃር ሚስጥራዊ ሕትመቶችን በማተም ብቸኛ ድርጅት ሲሆን፤ በአዲስ አበባና በአዋሣ ከተማ ቅርንጫፍ የሥራ መቀበያ ቢሮዎችንና የጽሕፈት መሣሪያ መደብሮችን በመክፈት የተለያዩ የሕግ መፃሕፍት፤ ነጋሪት ጋዜጦችንና ሌሎች የጽሕፈት መሣሪያዎች ሽያጭ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ለህትመት ሥራዎች. . .

የሕግ መፃሕፍት

በአዲስ አበባና በአዋሣ ከተማ የጽሕፈት መሣሪያ መደብሮች የተለያዩ የሕግ መፃሕፍት፤ ነጋሪት ጋዜጦችና ሌሎች የጽሕፈት መሣሪያዎች በሽያጭ ላይ ይገኛል፡፡

በሽያጭ ላይ የሚገኙ

ህትመት ቴክኖሎጂ

በአንጋፋው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የተቋቋመው የብርሃንና ሠላም የህትመት ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ስልጠና ኤጀንሲ እውቅና አግኝቷል

(COC) የምዘና ጣቢያ