የብ.ሰ.ማ.ድ. ሥራ አመራር ቦርድ በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የሥራ  ጉብኝት አደረገ

የሥራ አመራር ቦርዱ ጉብኝት  በድርጅቱ የተከናወኑትን የማሻሻያ ሥራዎች ላይ ያተኮረ ነበር፡፡

ግንቦት 8 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደው የሥራ አመራር ቦርዱ የሥራ ጉብኝት የድርጅቱ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ወርቁ ጓንጉልን ጨምሮ ክቡራን የሥራ አመራር ቦርድ አባላት፤ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሽታሁን ዋለ እና የማኔጅመንት አባላት ተገኝተውበታል፡፡

የሥራ አመራር ቦርዱ ያደረገው የሥራ ጉብኝት በድርጅቱ የተከናውኑ የማሻሻያ ሥራዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን በተለይ በአዲስ መልክ የተሰራውን የምስጢራዊ ህትመት ክፍል ሰፋ ያለ ጉብኝት ተደርጎበታል፡፡ በተመሳሳይ እድሳት የተደረገለት ነባር ህንፃ እና ድርጅቱ ያስገባው ሶልና የህትመት ማሽን የጉብኝቱ አካል ነበሩ፡፡

በሥራ ጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ የድርጅቱ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ወርቁ ጓንጉል በድርጅቱ የተከናወኑ የማሻሻያ ሥራዎች አመርቂ እንደሆኑና የሠራተኞች የሥራ ተነሳሽነት እጅግ የሚበረታታና ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡