የተሸከርካሪዎች ጥገና ጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ለስራ የሚጠቀምባቸውን ልዩ ልዩ ተሸከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ አዲስ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 300.00 ከፍለው በመግዛት በድርጅቱ 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የፋይናንሻይልና የቴክኒካል የመጫረቻ ሠነዶቻቸውን በተለያየ ኢንቨሎኘ በማድረግ ማቅረብና ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ  አለባቸው፡፡ ጨረታው ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰአት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የፋይናንሸያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ሰነድ ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

 

 
ተ.ቁ የተሽከርካሪው አይነት ብዛት ምርመራ
1 አይሱዙ ፒክአፕ (የሞተር እድሳት) 1 07/00010-3-1044
2 ቢሾፍቱ ስቴሽን ዋገን (ጊር ቦክስ ካምቢዮ ብልሽት) 1 3-52817
3 ኒሳን ሚኒባስ (ጊር ቦክስ ብልሽት) 1 /07/0013-3-10495
4 ቶዮታ ሚኒባስ (የሞተር ብልሽት) 1 /07/0009-3-10493
5 ፓጃሮ ሚስቲቡሺ (የሞተር ብልሽት) 1 3-14663
6 ሃዩንዳይ አክሰንት 1 3-10294
7 ቶዮታ ኮሮላ 1 3-10821