የደንበኞች እርካታ ማመሳከሪያ የመነሻ ጥናት አገልግሎት . . .ግዥ

ድርጅታችን አሁን በስራ ላይ ያለውን የድርጅቱን የገበያ አሰራርና የደንበኞች አያያዝ ሁኔታ በመፈተሽ የበለጠ ለደንበኞች አመቺ እንዲሆን በማድረግ በየስራ ክፍሎቹ በደንበኞች አያያዝ ላይ ችግር የሚፈጥሩ አሰራሮችን በማጥናት ለይቶና አስወግዶ ደንበኞችን ይዞ ለማቆየት የሚረዳ ደንበኛ ተኮር አሰራር በመዘርጋት፣ የደንበኛ እርካታን ለማሳደግና በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቆየት የሚያስችለውን የደንበኞች እርካታ ማመሳከሪያ የመነሻ ጥናት አገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው፣ በሚፈለገው የሥራ ዘርፍ ተዛማጅ የስራ ልምድ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ አዲስ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 300.00 ከፍለው በመግዛት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የፋይናንሻይልና የቴክኒካል የመጫረቻ ሠነዶቻቸውን በተለያየ ኤንቨሎኘ በማድረግ ማቅረብና ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡ ጨረታው ታህሳስ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰአት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የፋይናንሸያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት  ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡