Chief executive office

ዓላማ  

የማተምያ ድርጅቱን አቅም በማጐልበት የአሠራር ሥርዓቱን ማሻሻልና መለወጥ ማተሚያ ድርጅቱን በህትመት ኢንዲስትሪው ዘርፍ ብቁ ተወዳዳሪና መሪ እንዲሆን ማስቻል ምርታማነትንና ትርፋማነትን ማሣደግ የደንበኞችንና የባለድርሻ አካላትን እርካታ መጨመር  በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን እና ከሥራ አመራር ቦርድ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የድርጅቱን የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ዕቅድ ማውጣት፣ መምራት፣ ማስተባበር፣መቆጣጠርና ማስፈጸም፤

ዋና ዋና ተግባራት

  • ማተሚያ ድርጅቱ ስትራቴጂክ ዕቅድ መሠረት በማድረግ የሀገሪቱን ራዕይና እሴቶች የተጋራ በህትመት ኢንዱስትሪው ዘርፍ ብቁ ተወዳዳሪና መሪ እንዲሆን ማስቻል

  • የማተሚያ ድርጅቱን የአመራር አቅም ማሳደግ

  • በማተሚያ ድርጅቱ መልካም አስተዳደርን በማስፈን አፈፃፀሙ ውጤታማ መሆኑን ማረጋገጥ ምርታማነትንና ትርፋማነትን ማሳደግ

  • የደንበኞችንና የባለድርሻ አካላትን እርካታ መጨመር

  • ማተሚያ ድርጅቱ ማህበራዊ ኃላፊነቱን የሚወጣ ተቋም እንዲሆን ማድረግ