የህዝብ ግንኙነትና ማህበራዊ ጉዳዮች ፅ/ቤት ተግባርና ኃላፊነት
-
በማንኛውም ዓይነት መንገድ ተዘጋጅተው አገልግሎት ላይ የሚውሉ መረጃዎች ማሰባሰብና በተሟላ መልኩ አደራጅቶ መያዝ ፡፡ ክልከላ ከተደረገባቸው መረጃዎች በስተቀር፤ በተጠቃሚዎች የሚጠየቀውን ትክክለኛና ግልፅ የሆነ መረጃ በወቅቱ መስጠት፡፡
-
የመረጃ ማዕከል ማደራጀት፣ የተሰበሰቡትን መረጃዎች መለየትና ማደራጀት፣ መረጃዎችን በነጠላና በጥራዝ ማዘጋጀት፣ መረጃዎችን በሶፍት ኮፒ ማደራጀት፣
-
በዋና ዋና ተግባራት ዙሪያ ስለሚኖሩ ውይይቶችና የልማት ተግባራት በድምፅና በምስል/ ፎቶ ግራፍ/ መረጃዎችን መያዝ፣ ማደራጀት፣ ዶክመንት ማድረግ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለህዝብ ግንኙነት ሥራ በቪዲዮና በፎቶ መረጃዎችን በማጠናቀር ሥራ ላይ ማዋል፤
-
በአዋጅ ቁጥር 590/ 2000 ክፍል ሦስት የመገናኛ ብዙሃንና የመረጃ ነፃነት ትግበራ መሠረት ሊከናወኑ የሚገባቸውን መፈፀም ፡፡
-
የድርጅቱ የእቅድ አፈፃፀም በሥራ አመራር ኮሚቴ ተገምግሞ እንደቀረበ፤ የየወሩን፤ የየሩብ ዓመቱን፤ የ6 ወራቱን፤ ዓመታዊ በተጨማሪም በሕትመት ኢንዱስትሪው ያለውን እንቅስቃሴ ክትትል በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ዜና ብርሃንና ሰላም በማዘጋጀት ለውስጥ ሠራተኞች እንዲሁም በዜና መፅሔትና በዓመታዊ መፅሔት መረጃዎች ለውስጥ ለሰራተኞች፣ ባለድርሻ አካላትና ደንበኞች እንደደርሱ ማድረግ፤ ሲፈቀድም ጋዜጣዊ መግላጫ መስጠት፣
-
ስለድርጅቱ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ዓላማ፣ ግብ እና ፕሮግራም እንዲሁም የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች አስመልክቶ ለደንበኞች እና አጋር አካላት በመገናኛ ብዙኃን እና አግባብነት ባላቸው ሌሎች የመገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም ግንዛቤ የሚያስጨብጥ መረጃ መስጠትና ማሰራጨት፤
-
ቃለ ምልልሶች፣ የሁነቶች ፣ጉብኝትና ሌሎችም ከዕቅድ ውጭ የሚያጋጥሙ ተግባራት እንዲዘጋጁ ማድረግ፡፡
-
እንደአስፈላጊነቱ ሚዲያዎችን በመጋበዝ ስለ ድርጅቱ አፈፃፀምና ሂደት ቃለ- መጠይቅ እንዲሠራ ማመቻቸት፤
-
በድርጅቱ ድረ-ገፅና ማህበራዊ ሚዲያ ሊገለፁ የሚገቡ መረጃዎችና መልዕክቶች ወቅታቸውን ጠብቀው መጫን ፡፡
-
ድርጅቱን አስመልክቶ በሕትመት፣ በኤሌክትሮኒክስና በማኅበራዊ ድረ ገፆች የሚወጡና የሚተላለፉ ልዩ ልዩ ፕሮግራሞችን ክትትል ማድረግ፣ የተላለፉት ጉዳዮች ምላሽ የሚፈልጉ ወይም ሊገለፁ የሚገባቸው ጉዳዮች ከሆኑ ምላሹ ወይም ማብራሪያው ተዘጋጅቶ በሚሰጠው አመራርና በሚመረጠው ሚዲያ ለአንባቢዎች ለአድማጮችና ለተመልካቾች ማቅረብ፣
-
ከሚዲያ ጋር የጠበቀና መልካም የሥራ ግንኙነት በመመስረት አስተማማኝና ቀጣይነት ያለው የሚዲያ ሽፋን ለማግኘት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ማድረግ፤
-
ከደንበኞች ጋር የሚደረጉ ውይይቶችን፣ ከሠራተኞች ጋር የሚፈጠሩ መድረኮችን ማደራጀት፣ ማመቻቸት፣ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች እንዲሟሉ ማድረግ፤
-
የድርጅቱን የማህበራዊ ሃላፊነት ተሳትፎዎች የሚገልፁ ተግባራትን ማስተባባር እና አፈፃፀማቸው ክትትል ማድረግ፡፡