ዓላማ
በድርጅቱ የሥርዓተ ፆታ አቅም ለማሳደግና በሀገሪቱ የሚወጡ የሥርዓተ ፆታ ሕጎች፣ ደንቦችና አሠራሮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ሙያዊ እገዛ ለማድረግ
ዋና ዋና ተግባራት
- በድርጅቱ ውስጥ የሥርዓተ ፆታ ጉዳይ ተቋማዊ ማድረግ እና የልማት አገልግሎቶች ትኩረት እንዲያገኙ /gender sensitive/ ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፣
- በድርጅቱ ውስጥ የሥርዓተ ጾታ አቅም እንዲያድግ ያደርጋል፤
ዝርዝር ተግባራት
- ድርጅቱ በሀገሪቱ የሚወጡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከሥርዓተ ፆታ ጋር የተያያዙ ህጎች፣ ፖሊሲዎች፣ ደንቦችና አሠራሮች ላይ የበኩሉን አስተዋፅኦ በማበርከት የሥርዓተ ፆታ እኩልነትን እንዲያሳድግ ለማስቻል እገዛ ያደርጋል፣
- በድርጅቱ የሥርዓተ ፆታ አቅም ለማሳደግ ይተጋል፣
- ለስትራቴጂክ ዕቅድ ዝግጅት የተሟላ የክፍሉን መረጃ/ግብዓት ይሰጣል፤
- ድርጅቱ የሰው ኃይል የውስጥ አሠራር ሥርዓተ ፆታን “Mainstream” ያደረገ አሰራር እንዲኖር ሙያዊ እገዛ ያደርጋል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤ የሰው ኃይል የውስጥ አሠራር ሥርዓተ ፆታ እንዲያድግ የሚያስችል የአሠራር ማንዋል ያዘጋጃል፤ በአፈፃፀም ላይ ክትትል ያደርጋል፤
- ለድርጅቱ ሰራተኞችና የሥራ መሪዎች ተከታታይ የሥርዓተ ፆታ ሥልጠናዎች ያዘጋጃል፣ ከሚመለከተው አካል/ክፍል ጋር በመሆን ይሰጣል፣ ያሰጣል፣
- የሚዘጋጁ የሥልጠና ማኑዋሎች የሥርዓተ ፆታን ያገናዘቡ ስለመሆናቸው በየጊጊው ይገመግማል፤
- ስርዓተ ፆታን አስመልክቶ የማሰልጠኛ ማቴሪያል ዝግጅት ላይ ይሳተፋሉ፣ በምርምርና በማማከር ሥራዎች ላይ ይሳተፋል፡፡ በተጨማሪም በሌሎች የምክር፣ የሥልጠና የምርምር ሥራዎች ላይ ይሳተፋል፤
- የሥልጠና ፍላጎት ዳሰሳ ጥናቶች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሥርዓተ ፆታ ጉዳዮችን መዳሰሳቸውን ይከታተላል፣ ድጋፍ ይሰጣል፤
- ሥርዓተ ፆታን ያማከለ የድርጅት ፖሊሲ እንዲኖር ያደርጋል፣ የድርጅቱ መመሪያዎች ደንቦች የሥርዓተ ፆታን ጉዳይ ያካተቱ እንዲሆን ሙያዊ እገዛ ያደርጋል፤
- ድርጅቱን በመወከል በሚወጡ ህጎች ላይ ከሥርዓተ ፆታ ጋር በተያያዘ ሙያዊ ትንታኔዎችን ይሰጣል፤
- ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ጋር በመሆን የደንቦችና አሰራሮች አወጣጥና አፈጻጸም ላይ ክትትልና ድጋፍ ይሰጣል፤
- በዓላማ ቁጥር 2 ላይ የተገለፁትን ተግባራት፣ ውጤቶችና ልምዶችን ለድርጅቱ በየጊዜው ያሳውቃል፤
- እንደ አስፈላጊነቱ ለድርጅቱ ሰራተኞች የሥርዓተ ፆታ ስልጠና ፕሮግራም ያዘጋጃል፣ ይሰጣል፤
- የልምድ ልውውጥ በማድረግ አዳዲስ ግኝቶችን ወደ መስሪያ ቤቱ ያመጣል፤
- የአሰራር ማሻሻያ ሥርዓቶችን ተፈጻሚ ያደርጋል፤