Legal Services

ዓላማ

ድርጅቱ ሥራውን በተመለከተና በማንኛውም ጊዜ የሚፈጽማቸውን ውሎች፣ስምምነቶችን ማማከር፣ ድርጅቱ በማንኛውም ጉዳይ ፍርድ ቤት ስሙ እንዳይሄድና ከተከሰሰም አግባብነት ባለው የህግ የበላይነት፣ ጥራቱን የጠበቀና ፍትሃዊ ውሳኔ እንዲያገኝ ማድረግ፤ 

ዋና ዋና ተግባራት

    • ድርጅቱ ለሚዋዋላቸው ውሎችና ስምምነቶች ላይ የማማከር አገልግሎት ይሰጣል፤
    • ድርጅቱ ሲከሰስ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በማደራጀት ሙሉ መልስ ይሰጣል፤
    • ለድርጅቱ ሰራተኞችና ኃላፊዎችና የመብትና ግዴታ ምንነት እንዲረዳ ስልጠና ይሰጣል፤

 ዝርዝር ተግባራት

      • የሥራ ሂደቱን ተግባራት ያቅዳል፣ያፀድቃል፣ ያደራጃል፣ ይመራል፣ ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል፤
      • ለስትራቴጂክ ዕቅድ ዝግጅት የተሟላ የክፍሉን መረጃ/ግብዓት ይሰጣል፤
      • የድርጅቱ ስራዎች በህግ አግባብ መሰረት መከናወናቸውን ያረጋግጣል’ አግባብ ካላቸው ህጎች ውጪ የሚከናወኑ ተግባራት እንዳይኖሩ ይከታተላል፤
      • ተዘጋጅተው ለውሳኔ የቀረቡ የህግ መረጃዎችን ይገመግማል፣ ከህግ አንèር ያላቸውን ጥራትና ደረጃ ይፈትሻል፤
      • ድርጅቱ የሚቀርèቸው ፖሊሲዎች፣ ውስጠ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ አሰራሮች፣ ማኑዋሉችና ሌሎች ሰነዶች አግባብ ካላቸው ህጎች ጋር የተጣጣሙ መሆኑንና ከህግ አንፃር የሚያስከትሏቸውን እንድምታዎች ይገመግማል፣ ይፈትሻል፣ ይተቻል፣ ተገቢ የማሻሻያ ሀሳቦችን ያቀርባል፤
      • የድርጅቱን ንብረቶች የኢንሹራንስ ዋስትና ከህግ አንፃር ይመረምራል
      • ከስሩ ያለው ሰራተኛ በየዕለተለት ሥራ ላይ መሆኑን ይቆጣጠራል፣ ሪፖርት ያደርጋል፤
      • በውጭም ሆነ በውስጥ በሚቀርቡ የምርመራ ሪፖርቶች ላይ የተሰጡ የማሻሻያ ሀሳቦችና የአሠራር ድክመቶች ከህግ አንፃር ከሚያስከትሉት ውጤት አንፃር በወቅቱ እንዲታረሙ ያደርጋል፣ ይከታተላል፤
      • አዋጆች፣ የድርጅቱ ደንቦች እና መመሪያዎች አፈèçም ይከታተላል’ ያረጋግጣል፤
      • በህግ ነክ ጉዳዮች ዙሪያ የድርጅቱን የሥራ አመራር ቦርድና ሥራ አመራር ያማክራል፤
      • ለስራ አመራር ቦርድና ለማኔጅመንት በቀረቡ ህግ ነክ ሪፖርቶች ላይ በሚሰጠው ውሳኔ መሰረት የእርምት እርምጃዎች መወሰዳቸውን ያረጋግጣል፣ ይከታተላል፤
      • ወቅታዊና ህጋዊ እርምጃ ባልተወሰደባቸው ጉዳዮች ላይ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ሃሳብ ያቀርባል’ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
      • የህግ ድጋፍና ምክር ለሚጠይቁ ደንበኞች አስፈላጊውን ድጋፍ እና የስራ ትብብር ያደርጋል፤
      • በፍርድ ቤቶች የሚወሰኑ’ ለትምህርትነት የሚያስፈልጉና በድርጅቱ ውስጥ ሊታወቁ የሚገቡ ጉዳዮችሲኖሩ የሚመለከታቸው የሥራ መሪዎችና ባለሙያዎች እንዲያዩዋቸው ያደርጋል፤
      • የስራ ሂደቱ የስራ ክንውን በተያዘው በጀት መሰረት መሆኑን ይከታተላል’ ያረጋግጣል፤
      • የሚዘጋጁ ክሶች’ መልሶች’ የመልስ መልሶችና ቃለ መሃላዎች ፍ/ቤት ከመቅረባቸው በፊት አግባብነት ያለው ህግ በሚያዘው መሰረት መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
      • ድርጅቱ በከሳሽነት ወይም በተከሳሽነት በሚቀርብበት ጊዜ ድርጅቱን በመወከል ተገቢ መግለጫዎችን ያዘጋጃል፣ ይከራከራል፤
      • አከራካሪ ጉዳዮችን በመከታተል ያስፈጽማል፣ ለዋና ሥራ አስፈጻሚ ሪፖርት ያቀርባል፤
      • የድርጅቱን ህግ ነክ ጉዳዮች በመመርመር፣ በመከታተልና በማጥናት ተደጋግመው የሚከሰቱ ህግ ነክ ችግሮች መንስኤዎችን ያጠናል፣ ችግሮች ከመከሰታቸው አስቀድሞ መከላከል የሚቻልባቸውን ዘዴዎች አጥንቶ ለውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፣ ተፈèሚነታቸውንና ውጤታማነታቸውን ይገመግማል ይከታተላል፤
      • በተደጋጋሚ ሥራ ላይ የሚውሉትን የድርጅቱ ህግ ነክ ሰነዶች ለይቶ በማጥናት እንደየጉዳዩ አግባብ ሊከለሱ (customize) የሚችሉ ስታንዳርድ ሰነዶችን አዘጋጅቶ ለሥራ ዝግጁ ያደርጋል፤
      • በስራ ላይ ያሉና በየጊዜው የሚወጡ ህጎችና ደንቦች በትክክል ስራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል’ ለዋና ሥራ አስፈጻሚ ሪፖርት ያቀርባል፤
      • የድርጅቱ ህግ ነክ ጽሁፎች’ ስምምነቶች’ ክሶች’ የፍርድ ውሳኔዎች የተሰጠባቸውን ሰነዶች’ ማስታወቅያዎችንና ሌሎች ህግነክ ሰነዶች በጥንቃቄ እንዲደራጁና እንዲያዙ ያደርጋል፤
      • ይግባኝ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ የይግባኝ ጊዜ ከማለፉ በፊት የይግባኝ ክስ መብቱ ለሚፈቅድለት ፍ/ቤት እንዲቀርብ ያደርጋል፤
      • ክርክር በእርቅ እንዲዘጋ አስፈላጊ ሲሆን ከከሳሾቹ ወይም ከተከሳሾቹ ጋር በመነጋገር እና በመወያየት ውጤቱን ለዋና ሥራ አስፈጻሚ ሪፖርት ያደርጋል፤
      • ድርጅቱ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር የሚያደርጋቸውን የግዥ’ የሽያጭና የመሳሰሉት ውሎችና ስምምነቶች ከህግ’ ከአዋጆች’ ከደንብና መመሪዎች አንፃር በመገምገም የህግ ድጋፍ ያላቸው እና የድርጅቱን ጥቅም የሚያስከብሩ ስለመሆናቸው/ ስለአለመሆናቸው አስተያየት ይሰጣል’ ያማክራል፤
      • የፍርድ ባለእዳዎችን ንብረት ያጣራM’ ßታ}LM፤
      • የባለእዳዎች ንብረት በፍ/ቤት እንዲያዝና እንዲከበር ያደርጋል፤
      • በክስ ምክንያት ለሚመጡ ወጪዎች ህጋዊ ደረሰኝ በመቀበል በየጉዳዩ ስም መዝግቦ ይይዛል፤
      • ከሰራተኛ ማህበሩ ጋር በሚደረጉ ድርድሮችና የህብረት ስምምነቶች ከህግ አንፃር የተሟሉና የሁለቱንም ወገን ጥቅም የሚያስጠብቁ ስለመሆናቸው’ ስለአገላለፃቸውም ሆነ ትርጉማቸው ግልጽና በድርጅቱ ላይ የተለየ ግዴታ የማያስከትሉ መሆኑን በመመርመር ለውሳኔ የሚረዳ አስተያየት ያቀርባል፤
      • የሥራ ሂደቱ ስራዎች በተቀመጠላቸው የሰዓት ልኬት (standard time) መሠረት መከናወናቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤
      • የማሰልጠን፣ የማብቃት እና ተተኪ የማፍራት (coaching and monitoring) ስራዎችን ያከናውናል፤
      • የሥራ ሂደቱን ዕቅድ፣ በጀት፣ የተለያዩ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርቶችን ያዘጋጃል፤
      • ለሥራ ዘርፉ በተያዘው በጀት መሰረት የስራ ክንውን መደረጉን ይከታተላል’ ያረጋግጣል፤

 ከቅርብ የሥራ መሪው በሚሰጠው አጠቃላይ የሥራ መመሪያና ትዕዛዝ መሰረት የሥራ ሂደቱን ሌሎች ተዛማጅ ተግባራት ይመራል፣ ያከናውናል፡፡