Finance Directorate

ዓላማ

የድርጅቱን ስትራቴጂክ ዕቅዶች የማዘጋጀት፣ ዕቅድን ከበጀት ጋር አጣጥሞ የመያዝና የማስፈፀም፣ የሥራ ሂደቱን በማሻሻልና በመለወጥ ምርታማነት የሚያድግበትን አሠራር የመቀየስ፣ ሠራተኞችን የማብቃት፣ የውስጥ አቅምን በማጎልበት የደንበኞችን ፍላጎት የማርካት፣ የድርጅቱን ሂሣብ የማስመርመር፣ የመንግሥት ግዴታዎችን የመጠበቅና፣ ጤናማ የሆነ የፋይናንስ አስተዳደር እንዲኖር ማድረግ አጠቃላይ የሥራ ሂደቱን የማስተባበርና የመምራት ኃላፊነት አለበት።

ዋና ዋና ተግባራት

  • የሥራ ሂደቱን ስትራቴጂክ ዕቅድ ማዘጋጀት
  • በጀት ያዘጋጃል፣
  • የሥራ ሂደቱን ይመራል፣ ያስተባብራል
  • የአሰራር ስርዓቱን ያሻሽላል፣ ይለውጣል
  • የድርጅቱን ፋይናሻል ሪፖርት ያዘጋጃል፣
  • ጤናማ የሆነ የፋይናንስ አስተዳደር አንዲኖር ያደርጋል፣
  • የድርጅቱን ሂሣብ በውጭ ኦዲተር ያስመረምራል፣ ወቅታዊም ያደርጋል፣

ዝርዝር ተግባራት

  • የሥራ ሂደቱን ተግባራት ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ይቆጣጠራል፤

  • ለተለያዩ የሥራ ሂደቶች የበጀት ጥሪ የማድረግ፣ የበጀት ጥያቄዎችን የመቀበል፣ ጠቅላላ ፋይናንሽያል በጀት የማዘጋጀት፣ አፈጻጸሙን የመከታተል፣ አፈጻጸሙ ከተያዘው በጀት ጋር በሚገባ ተነጻጽሮ ተገቢው ቁጥጥር መደረጉን የሚያሳይ የአፈጻጸም ሪፖርት የማቅረብ ሥራዎችን ይከታተላል፣ ያስተባብራል፤

  • ከሚመለከታቸው የሥራ ሂደቶች ጋር በመተባበር ልዩ ልዩ አዳዲስ የፕሮጀክት ሀሳቦችን ያመነጫል፣ ፕሮፋይል ያዘጋጃል፣ ተዘጋጅተው የቀረቡ ፕሮፋይሎችን በመመርመር አስተያየት ይሰጣል፣ የፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ከተቀመጠላቸው ዕቅድ አንጻር ይከታተላል፣

  • ልዩ ልዩ የማስፋፊያና የመተኪያ የኢንቨስትመንት አማራጭ ሀሳቦችን ያቀርባል፣

  • አስፈላጊ መረጃዎች እንዲሰባሰቡ በማድረግ የድርጅቱን ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ከሌሎች የሥራ ሂደቶች ጋር ያዘጋጃል፤

  • ለድርጅቱ ሥራ አመራር፣ ለሥራ አመራር ቦርድ፣ ለመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ፣ ወዘተ የሚቀርቡ ሪፖርቶች በሚፈለገው ጊዜ ተዘጋጅተው እንዲቀርቡ ያደርጋል፤

  • የድርጅቱን የአለፉት ዓመታት የዕቅድና ክንውን መረጃ የሥራ አፈèçሙን አካሄድ (trend) በሚያሳዩ የተለያዩ የመረጃ አቀራረብ ስልቶች ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ ያደርጋል፤

  • የሂደቱ ስራዎች በተቀመጠላቸው የሰዓት ልኬት (standard time) መሠረት መከናወናቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤

  • የማሰልጠን፣ የማብቃት እና ተተኪ የማፍራት (coaching and monitoring) ስራዎችን ያከናውናል፤

  • የዱቤ ሽያጭ ሂሳብ እና ማንኛውም የድርጅቱ ተሰብሳቢ ገንዘብ በተገባው የግብይት ውለታ መሰረት በአግባቡ፣ በወቅቱና በተሟላ መረጃ እንዲሰበሰብ፣ ለተሰብሰበው ገንዘብ የተሟላ መረጃ እንዲኖር፣ ከፋይናንስ አቋም አኳያ የድርጅቱ ቀጣይነት አስተማማኝ እንዲሆን፣ የድርጅቱ ገንዘብ በአግባቡ እንዲጠበቅና በመረጃ ተደግፎ ባንክ ገቢ እንዲደረግ በሚያስችሉ ተግባራት ላይ አመራር ይሰጣል፣ ይከታተላል፣ ያስተባብራል፤

  • የአሠራር ማሻ ሥርዓት ተፈፃሚነታቸውን ይከታተላል፣ተግባራዊ ያደርጋል፡ ያስፈጽማል፣

  • የጥቃቅን ወጪ፣ የአገልግሎትና ዕቃ ግዥ፣ የደመወዝና ሌሎች የሥራ ማስኬጃና የመደበኛ በጀት ክፍያ ጥያቄዎች ከመመሪያ፣ ከውል ስምምነት፣ ከሥራ ሰዓት ቁጥጥር፣ ከበጀት፣ ወዘተ አንጻር በአግባቡ ተመርምረው፣ ተረጋግጠውና ጸድቀው ክፍያ እንዲፈጸም ያደርጋል፤

  • የድርጅቱ የግብይት ሰነዶች (business documents) በአግባቡ በፋይል መደራጀታቸውን፣ የሂሳብ መለያ ቁጥር የተሰጣቸው መሆኑን፣ በትክክል መመዝገባቸውን፣ ወደ ዋናው ሂሳብ መዝገብ (ledger) ፖስት መደረጋቸውን፣ ለድርጅቱ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የመረጃ ፍላጎት የተሟላ መልስ መስጠት የሚያስችሉ ዕለታዊ፣ ሳምንታዊ፣ ወርሃዊ፣ የስድስት ወር፣ ዓመታዊ እና ሌሎች ወቅታዊ የፋይናንስ ሪፖርቶች (interim financial reports) የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርቶች አዘገጃጀትና አቀራረብ ስታንዳርድ (IFRS) መሰረት በወቅቱ ተዘጋጅተው መቅረባቸውን ያረጋግጣል፤

  • የድርጅቱን የንብረት ቆጠራ ሥራ የዝግጅት፣ የመቁጠር፣ የመመዝገብ፣ ቆጠራው በቀጥታ የሚመለከታቸውን አካላት (አስቆጣሪ፣ ቆጣሪና መዝጋቢ) የማፈራረም፣ የንብረት ዋጋ ትመና (inventory valuation) የማነስ ወይም የመብለጥ ልዩነቶችን የማስታረቅ፣ የመመዝገብ በአጠቃላይ ከቅድመ ዝግጅት እስከ ፍጻሜ ያለውን የንብረት ቆጠራ ሂደት የመምራት ሥራዎችን ያካሂዳል፤

  • ምዝገባው የተጠናቀቀን ዋና የሂሳብ መዝገብ (ledger) የሂሳብ ሚዛን (trial balance) መዘጋጀቱን እና አጠቃላይ የምዝገባው ትክክለኛነት መረጋገጡን፣ ሂሳብ መዘጋቱን፣ ወቅታዊ የፋይናንስ ሪፖርቶች መዘጋጀታቸውን ያረጋግጣል፤

  • በየስራ ዘመኑ መጠናቀቂያ የድርጅቱን የፋይናንስ አቋም መግለጫ (balance sheet statement)፣ የትርፍ/ ኪሳራ መግለጫ (profit /loss statement) ፣ የገንዘብ ፍሰት መግለጫት (cash flow statement) እና ሌሎች የሂሳብ መግለጫዎችን ያዘጋጃል፤ የሂሳብ መግለጫዎች በትክክል መዘጋጀታቸውን ያረጋግጣል፤

  • የድርጅቱን የሂሳብ ምዝገባ ክንውኖች ይፈትሻል፣ በሂሳብ ምዝገባው አጠቃላይ ዑደት (accounting cycle) በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራትን ትክክለኛነት ያረጋግጣል፣ የሂሳብ ምዝገባ ግድፈቶች ከተገኙ ተገቢው ማስተካከያ እንዲደረግ ያደርጋል፤

  • በዓለም አቀፍ የሂሳብ እስታንዳርድ ቦርድ/IASB/ አማካኝነት በየጊዜዉ የሚለቀቁ ወይም የሚሰረዙ እስታንዳርዶችን በመከታተል የሂሳብ ፖሊሲ ማኑዋሉን ወቅታዊ ማድረግና የምዝገባና ሪፖርቲንግ ሂደቱንም አዲስ ከሚመጣዉ እስታንዳርድ ጋር እንዲጣጣም ያደርጋል፡፡

  • በዓመታዊ የቌሚ ንብረት ቆጠራ አገልግሎት ላይ ሊዉሉ የማይችሉ/Damage/ የሆኑ ቌሚ ንብረቶች እንዲለዩ በማድረግና የጥገና ታሪካቸዉን በመመርመር የጉዳት መጠናቸዉን በመለካት/Impairment Testing/ አስፈላጊዉን የሂሳብ ማስተካከያ ያደርጋል፡፡

  • የድርጅቱን የፋይናንስ ሪፖርቶች በኦዲተር ያስመረምራል፣ በኦዲት ምርምራ በሚሰጥ ግብረ መልስ መሰረት ተገቢ የማስተካከያ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ያደርጋል፣ በኦዲት ምርመራው መሰረት የተስተካከለ ሪፖርት ተዘጋጅቶ እንዲወጣ ያደርጋል፣ ለተጠቃሚ ያቀርባል

  • የሥራ ሂደቱ ደብዳቤዎች፣ የግብይት ሰነዶች (business documents) የገንዘብ መቀበያ ደረሰኞችና የሂሳብ መዛግብት እና ሪፖርቶች በISO መመሪያና አሰራር መሰረት ተደራጅተው እንዲያዙ ያደርጋል፤

  • ለሥራ ሂደቱ ሥራ በግብዓትነት የሚያስፈልጉ ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች በተሟላ ሁኔታ እንዲቀርቡ ያደርጋል፣ አያያዛቸውንና አጠቃቀማቸውን ይከታተላል፤

  • የሥራ ሂደቱ የሰው ኃይል የሥራ ሰዓት አክብሮ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ ክትትል ያደርጋል፣ ያስተባብራል፣ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ያደርጋል፣ የሥራ አፈጻጸም ብቃታቸው በስልጠና መሻሻል የሚያስፈልጋቸው ተገቢውን ስልጠና እንዲያገኙ ያደርጋል፤

  • የድርጅቱ የሥራ እንቅስቃሴ አነስተኛ በሆነ ወጪ የሚካሄድበትን መንገድ አጥንቶ የማሻሻያ ሀሳብ ያቀርባል፣

  • ያለአግባብ የጥሬ ዕቃ ወጪና ክምችት እንዳይኖር ይከታተላል፤

  • ለሥራ ሂደቱ በሚሰጠው የስልጣን ውክልና መሠረት ልዩ ልዩ ክፍያዎችን ይፈቅዳል፣ ቼኮችን ይፈርማል፤

  • ለድርጅቱ የመሸጫ ዋጋ አወሳሰን አስፈላጊ የሆኑ የወጪ መረጃዎች ተዘጋጅተው ለውሳኔ እንዲቀርቡ ያደርጋል፤

  • ድርጅቱ የሥራ ማስኬጃ እጥረት ሲያጋጥመውና ለተጨማሪ ኢንቨስትመንት ገንዘብ እጥረት ሲኖር ከባንክ የአጭርና የረዥም ጊዜ ብድር እንዲያገኝ ጥረት ያደርጋል፤

  • የድርጅቱ የኮስቲንግ አያያዝ መመሪያ እንዲወጣና በየጊዜው እንዲሻሻል ያደርጋል፤

  • የድርጅቱ ንብረቶች የኢንሹራንስ ዋስትና እንዲኖራቸው ያደርጋል፣ በየዓመቱ መታደሱን ይከታተላል፤ የሚከፈሉ የካሳ ክፍያዎች ትክክለኛነታቸውን በማረጋገጥ እንዲሰበሰብ ያደርጋል፤

  • የድርጅቱን የገንዘብ አጠቃቀም ውጤታማነት የበለጠ ለማረጋገጥ የሚያስችል አሠራር ይቀይሳል፣ ሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፤

  • ከሥራ ሂደቱ የውጭና የውስጥ ደንበኞች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች መፍትሄ በማፈላለግ ውሳኔ ይሠጣል/እንዲሰጥ ያደርጋል

  • በተሰጠው የሥልጣን ውክልና መሠረት ከሥራ ሂደቱ ጋር ግንኙነት ካላቸው የተለያዩ አካላት ጋር የሥራ ግንኙነት ያደርጋል

  • ከዋና ስራ አስፈፃሚ እና ከምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ የሚሰጡትን ሌሎች ሥራዎች ይሠራል