ዓላማ
የድርጅቱን ስትራቴጂክ ዕቅዶች የማዘጋጀትና የማስፈፀም፣ የሥራ ሂደቱን በማሻሻልና በመለወጥ ምርታማነት የሚያድግበትን አሠራር የመቀየስ፣ ሠራተኞችን የማብቃት፤ የውስጥ አቅምን በማጎልበት የደንበኞችን ፍላጎት የማርካት፤ አጠቃላይ የሥራ ሂደቱን የማስተባበርና የመምራት።
ዋና ዋና ተግባራት
-
የሥራ ሂደቱን ስትራቴጂክ ዕቅድ ያዘጋጃል፤ ለደንበኞች የሚቀርቡ ሥራዎን ይገምታል ዋጋ ይሰጣል ፣ይቀበላል ሽያጭ ያከናውናል፡፡
-
ዕቅድ ያዘጋጃል ያስተባብራል ይቆጣጠራል፣
-
ይመራል፣ይተገብራል፣ዋጋ ይሰጣል፣
-
ስለገበያ ያጠናል ሐሳብ ያቀርባል፣ የፐብሊሺንግ ሥራን ያካሂዳል
-
ከፍተኛ የህትመት ሥራ ውሎችን ይፈራረማል
-
የሥራ ሂደቱን ይመራል፤ ያስተባብራል
-
የአሠራር ስርዓቱን ያሻሽላል፤ ይለውጣል፤ የድርጅቱን የሥራ ደረጃ ይከታተላል ይገመግማል፣ መፍትሔ ይሰጣል፡፡
ዝርዝር ተግባራት
-
በድርጅቱ የስትራቴጂክ ዕቅድ አጠቃላይ ውሳኔ በሚሹ ጉዳዮች ላይ ይሣተፋል
-
የድርጅቱን ስትራቴጂያዊ ዕቅድ፣ አጠቃላይ የማምረት አቅም እንዲሁም የገበያውን ፍላጐት በማገናዘብ ሥራዎችን ያቅዳል፤
-
የዋና ሥራ ሂደቱን ስትራቴጂክ ዕቅድ ያዘጋጃል
-
በደንበኛ አገልግሎትና ግራፊክ ዲዛይን ዋና የሥራ ሂደት የሥራ ዋጋ መስጠት፣የሥራ መቀበልና ሽያጭ፣የግራፊክ ዲዛይን የዕቅድና ክትትል ሥራዎችን ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል፤
-
ሽያጩን ለማጐልበት አጥንቶ በሚያቀርበው፣ በደንበኛ የሥራ ትዕዛዝ በተጠየቀው ዝርዝር መስፈርት እና በተያዘለት ጊዜ ተሰርቶና ተጠናቆ መቅረቡን ያረጋግጣል፣ የተቀላጠፈ የደንበኛ አገልግሎትና አያያዝ ይፈጥራል፤ የሽያጭ አውታሮችን ያስፋፋል፣
-
በሥራ ሂደቱ ላሉት ሠራተኞች የምክር አገልግሎት ይሠጣል፣ ያሰለጥናል፣ ያበቃል
-
በሥራ ሂደቱ የሚገኙ ሠራተኞችን የሥራ አፈፃፀም ይገመግማል
-
የሥራ ሂደቱን በመወከል ከፍተኛ የህትመት ውሎችን/ስምምነቶችን ይፈራረማል
-
ከፍተኛ የህትመት ጨረታ በሚኖርበት ጊዜ የጨረታ(Virtual) ኮሚቴ እንዲቋቋም በማድረግ ጨረታውን ይመራል
-
የአሰራር ስርዓቱን ያሻሽላል፤ እንደ አስፈላጊነቱ ይለውጣል
-
የአሰራር ስርዓቱን ተግባራዊ ያደርጋል ተፈጻሚነታቸዉን ይከታተላል::
-
ከሥራ ሂደቱ ውጭና የውስጥ ደንበኞች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች መፍትሔ በማፈላለግ ውሳኔ ይሠጣል/እንዲሰጥ ያደርጋል
-
በሥልጠና ሂደት አፈፃፀም ከሠው ሀብት አመራር ደጋፊ የሥራ ሂደት ጋር በመተባበር ይሠራል
-
የሥራ ሂደቱን ይመራል፤ ያስተባብራል
-
ከዋና ስራ አስፈፃሚ እና ከምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ የሚሠጡትን ሌሎች ድርጅታዊ ሥራዎች ይሠራል