ዓላማ
የድርጅቱን ስትራቲጅክ ዕቅድ በጋራ በመንደፍ የስራ ሂደቱን ዕቅድ ግብ የማስፈፀም ስልት ማዘጋጀት የሥራ ሂደቱን መምራት ማስተባበር እና መቆጣጠር
ዋና ዋና ተግባራት
- የሥራ ሂደቱን ስትራቴጂ ዕቅድና ግብ የማስፈፀሚያ ስልት ማዘጋጀት
- የአሰራር ስርዓት ማሻሻያዎችን ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል
- ከውስጥና ከውጭ ደንበኞች ጋር የተጠናከረ የሥራ ግንኙነት መፍጠር
- የሥራ ሂደቱን በተለያዩ መድረኮች መወከል
- የሥራ ሂደቱን መምራት
- የባለድርሻ አካላትን የደንበኞች እርካታ ማሳደግ
- የተሽከርካሪ ዓመታዊ የብልሽት መከላከል ጥገና ኘሮግራምና በጀት እንዲያዝ ያደርጋል፡፡
- የሲቭል ስረዎችን የጥገነና አዳዲስ ስራዎችን ግንባታ በተመለከተ በጀት እንዲያዝ በማድረግ አፈጻጸማቸውን ተግባራዊ ማድረግ፡፡
ዝርዝር ተግባራት
-
በዳይሬክቶሬቱ ስር ያሉትን ቡድኖች ያደራጃል፣ ተግባራቸውን ያቅዳል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል፤
-
የሥራ ሂደቱን ስትራቴጂክ ዕቅድ ያዘጋጃል በአግባቡ ስራ ላይ መዋላቸውን ይቆጣጠራል፣ያረጋግጣል
-
የቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶች በአግባቡ በጥቅም ላይ መዋላቸውን ይቆጣጠራል፣ያረጋግጣል፤
-
ለሥራ ሂደቱ በአፈፃፀሙ የላቀና ተወዳዳሪነትን የሚያመጣ ስልት ይቀይሳል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፣ ውጤታማነቱንም ይገመግማል፣ ያረጋግጣል፣
-
የስራ ሂደት መመሪያዎች በስሩ ላሉ ቡድኖችና ሠራተኞች ያስተላልፋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
-
የድርጅቱን የአቅርቦትና ሎጀስቲክ የዋናና ደጋፊ የሥራ ሂደቶች ሥራዎች ያለማቋረጥ በፕሮግራም እንዲካሄድ ለማድረግ በቂ ጥሬ ዕቃዎች፣ መለዋወጫዎችና አላቂ ዕቃዎች በበቂ ክምችት መኖራቸውን ያረጋግጣል፤
-
ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ሀገር የሚገዙ ማናቸውም ዓይነትቋሚና አላቂ ዕቃዎችና አገልግሎቶች የግዥ ደንብና ሥርዓቶችን የተከተሉ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
-
የግዥ ክፍያዎች በወቅቱና በውለታው መሠረት መከናወናቸውን ይከታተላል፤
-
ተገዝቶ የሚቀርበው ዕቃ በጥያቄው ዝርዝር መግለጫ መሠረት መሆኑን ይከታተላል፣ እንዲረጋገጥ ያደርጋል፤
-
ለአቅርቦት ክፍያ የሚያስፈልጉ መረጃዎችና ሰነዶች ተጠናቀው /ተሟልተው/ ለበጀትና ፋይናንስ የሥራ ሂደት እንዲቀርቡ በማድረግ ክፍያዎች በወቅቱ መፈፀማቸውን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
-
የመድህን ዋስትና፣ የጉምሩክ፣ የወደብ ፎርማሊቲዎችና የባንክ ክፍያዎች በወቅቱ እንዲፈፀሙ በማድረግ የግዥውን ሂደት ያፋጥናል፣ ይቆጣጠራል፤ ለጠፉ ለተበላሹና ከጥቅም ውጭ ለሆኑ ዕቃዎች በተገባላቸው የመድህን ዋስትና ሽፋን መሠረት ካሳ በወቅቱ እንዲከፈል ከሚመለከተው የመድህን ዋስትና ድርጅት ጋር በመነጋገር ያስፈፅማል፣ ይቆጣጠራል፤
-
ከነባርና አዲስ አቅራቢዎች ጋር የአጭር የረዥም አቅርቦት ውል በመግባትና የሰመረ ግንኙነት በመፍጠር ድርጅቱ የተሻለ ዋጋ እንዲያገኝ ይጥራል፣ ተጨማሪ አቅራቢዎችን በማፈላለግ የተሻሉ አማራጮችን ያመቻቻል፤
-
የአገር ውስጥና የውጭ አገር ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር መረጃዎች እንዲያዙ በማድረግ የግዥው ሂደት በትክክል መፈጸሙን ክትትል ማድረግ፡፡
-
የድርጅቱ ንብረቶች ከአደጋ፣ ከብልሽት እና ከስርቆት ተጠብቀው በአግባቡና በጥንቃቄ እንዲያዙ ያደርጋል፤
-
የድርጅቱ ንብረት ቆጠራ በወቅቱና በትክክል መካሄዱን ይከታተላል፣ ንብረት ቆጠራ ሲደረግ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፤በምዝገብና በቆጠራ መካከል ልዩነት ሲኖር ሁኔታው እንዲጣራ ያደርጋል፣ አስፈላጊውን የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፤
-
የምርት ሥራ እንቅስቃሴ እንዳይስተጓጎል በድርጅቱ የዝቅተኛና ከፍተኛ ስቶክ መጠን ፖሊሲ መሠረት በቂ ክምችት መያዙን ያረጋግጣል፣ ለየሥራ ሂደቱ የተገዙ ዕቃዎች በአግባቡ ለተጠቃሚዎች መድረሳቸውን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
-
ለድርጅቱ አገልግሎት የማይውሉ ንብረቶች በወቅቱ በሽያጭ፣ በስጦታ፣ በመቅበርና በማቃጠል እንዲወገዱለሚመለከተው የመንግስት የኬሚካል ፍሳሽ አስወጋጅ ሪፖርት እንዲቀርብ ያደርጋል፣ ይገመግማል፣ ያስገመግማል፣ ይወስናል፣ ያስወስናል፣ በመመሪያው መሠረት እንዲወገድ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
-
የአገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሀገር ግዥዎች የድርጅቱን የውጭ ምንዛሬና የፋይናንስ አቅም በማገናዘብ የድርጅቱን ጥቅም በማይጐዳ ሁኔታ በዓመት አንድ ጊዜ በጨረታ እንዲወጣ በማድረግና ከአሸናፊዎች ጋር ውል በመፈራረም በሚዘጋጀው የግዥ መርሐ ግብር መሠረት በወቅቱና በተፈለገው ዓይነትና መጠን እንዲቀርብ ክትትል ያደርጋል፣ ይቆጣጠራል፤
-
ለሥራ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን እንዲሟሉ ያደርጋል
-
አዳዲስ አሰራሮችን በመንደፍ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል
-
በተሰጠው የሥልጠና ውክልና መሰረት ግዥዎችን ያፀድቃል/የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል
-
የአመራርና የአቅም ክፍተት በማየት የብቃት ማጎልበቻ ፕሮግራም ይቀርፃል
-
የድርጅቱ ስትራቴጂ ለማስፈጸም የሚረዱ ፕሮግራሞችን ይቀርፃል ይተገብራል
-
የሥራ ሂደቱን አጠቃላይ የሥራ አፈፃፀሞች፣ ያጋጠሙ ችግሮች ከነመፍትሄ ሀሳቦች ሪፖርት አዘጋጅቶ ለምክትል ስራአስፈጻሚ የድጋፍ ዘርፍ ያቀርባል፤
-
የሥራ ሂደቱን ሌሎች ተዛማጅ ተግባራት ያከናውናል፣ያስተባብራል፣ ያስፈéማል፡፡
-
ለማዕከልና ለመስክ ስራ የሚውሉትን ተሽከርካሪዎች እንዲለዩ ትዕዛዝ ያስተላልፋል፤
-
በመስክም ሆነ በከተማ ብልሽት ያጋጠማቸውን ተሽከርካሪዎች ለጥገና ክፍል በማሳወቅ ጋራዥ ገብተው እንዲጠገኑ ያደርጋል፤
-
ለጥገና የሚያስፈልገውን ስልጠና በመለየት እንዲሰለጥኑ ያደርጋል፡፡
-
የአሰራር ስርዓት ማሻሻያዎችን ተግባራዊ እንዲሆን መከታተል፤ እና ማስፈጸም ፡፡
-
በተጨማሪም ከቅርብ ኃላፊው በሚሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡