ተግባርና ኃላፊነት
-
በድርጅቱ አጠቃላይ ደንብና መመሪያ መሰረት በስሩ የሚገኙ የጥገና ቡድኖች ሥራዎች ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ይመራል፣ ያስተባብራል፤
-
የድርጅቱን የህትመት መሳሪያዎች የመከላከልና የብልሽት ጥገና ሥራዎች በበላይነት ይመራል፣ ያስተባብራል፤
-
በድርጅቱ አጠቃላይ የሥራ ዕቅድና በጀት ዝግጅት እንዲሁም የፖሊሲ ቀረጻ ሥራዎች ላይ የሥራ ሂደቱን ወክሎ ይሳተፋል፤
-
የማምረቻ ማሽኖች አስፈላጊው የጥገና ታሪክና የአገልግሎት ዘመን መረጃዎች እንዲኖራቸው ያደርጋል፤
-
ለሥራ ሂደቱ የሥራ ዘርፎች የሚያስፈልገው የሰው ኃይል፣ የጥገና መገልገያ መሣሪያዎች፣ መለዋወጫዎችና ሌሎች መሰል ግብዓቶች በሚፈለገው ዓይነት፣ መጠንና ጥራት መሟላታቸውን ያረጋግጣል፤
-
ድርጅቱ አዳዲስ መሳሪያዎችንና መለዋወጫዎችን ለመግዛት ሲወስን ቴክኒካል ስፔስፊኬሽን በዘርፋ ባለሙያዎች እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ በቴክኖሎጂ መረጣና በመሳሰሉት ጉዳዮች አስፈላጊውን ሙያዊ ዕገዛ ያደርጋል፣ ግዥ በዚሁ መሰረት መከናወኑን እየተከታተለ ያረጋግጣል፤
-
የሥራ ዘርፉ ምርታማነት የሚሻሻልበትንና የሚያድግበትን ሁኔታ እንዲሁም የአሰራር ዘዴው በየጊዜው ካለው የቴክኖሎጂ ዕድገት ጋር አብሮ የሚራመድበትን መንገድ በማጥናት የሚቀርቡ የማሻሻያ ሀሳቦችን በመገምገም ለድርጅቱ የሥራ እንቅስቃሴ ዕድገት የሚያግዙ ቴክኒክ ነክ የማሻሻያ የጥናት ውጤቶችን በመለየት ተግባራዊ እንዲሆኑ ከአስተያየት ጋር ለውሳኔ ያቀርባል፤
-
በሥራ ሂደቱ የሥራ ዘርፎች የሚቀርቡ የአቅርቦት እና የውጭ ጥገና ጥያቄዎች አግባብነታቸውን በማረጋገጥ ያጸድቃል፣ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፤
-
የህትመት መሣሪያዎችን የቴክኖሎጂ ደረጃ ይከታተላል፤ የማተሚያ ድርጅቱን የመሣሪያ አጠቃቀምና ውጤታማነት ለማሻሻል የሚረዱ ዘዴዎችን ይቀይሳል፣ በተግባር እንዲውሉ አስፈላጊውን ጥረት ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ የሥራ ሂደቱን ተግባራት ለማሻሻል የሚረዱ ምርምሮችን ያካሂዳል፣ በሚገኘው ውጤት መነሻነትም የታመነባቸውን የአሰራር ለውጦች ተግባራዊ ያደርጋል፤
-
የሥራ ሂደቱ ባለሙያዎች ተገቢውን የሥራ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉና የኢንዱስትሪያል ሴፍቲ ህጐችን እንዲያከብሩ መመሪያ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፤
-
የመለዋወጫዎች አጠቃቀም ከብክነት የጸዳና በቁጠባ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ያረጋግጣል፣ ይቆጣጠራል፤
-
የህትመት መሣሪያዎችን አያያዝና አጠቃቀም አስመልክቶ የወጡ ልዩ ልዩ መመሪያዎች፣ ማኑዋሎችና ቅጾች በጥንቃቄ እንዲያዙና እንዲከበሩ ያደርጋል፣ ሥራ ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል፤
-
የሥራ ሂደቱን አጠቃላይ የሥራ ዕቅድና አመታዊ በጀት ከሥራ ሂደቱ የሥራ ዘርፎች የሚቀርቡ መረጃዎችን በማጠናቀር ያዘጋጃል፤ በድርጅቱ አጠቃላይ ዕቅድ ውስጥ ተካቶ ተግባራዊ እንዲደረግ በመወሰን ሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፤
-
አዳዲስ የማምረቻ መሣሪያዎች እና የድጋፍ ሠጪ መሣሪያዎች ተገዝተው ሲመጡ ተከላውን ያቅዳል፣ ያስተባብራል፤ ከተተከሉም በኋላ በትክክል መሰራታቸውን ያረጋግጣል፤
-
በእርጅና ምክንያት በማምረት አቅም ደካማነት ወይም በመለዋወጫ ዕቃ ዕጦት ከአገልግሎት ውጪ በመሆን ላይ የሚገኙ የማምረቻ መሣሪያዎች ከምርት ላይ የሚወገዱበትን ሂደት የአፈጻጸምና የጊዜ ሰሌዳ ያወጣል፤
-
በሥራ ሂደቱ የሚገኙ ባለሙያዎች የሥራ ብቃታቸውንና ሙያቸውን እንዲያዳብሩና እንዲያሻiሉ በየወቅቱ የሙያ ማሻሻያ ስልጠናና ትምህርት ሊያገኙ የሚችሉበትን መንገድ በማጥናት ሥራው በማይበደልበት ሁኔታ ፕሮግራም በመያዝ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
-
በስሩ የሚገኙ የሥራ ኃላፊዎችን የሥራ አፈጻጸም ይገመግማል፣ ለዚሁ ሥራ የተዘጋጀውን ቅጽ ይሞላል፤
-
የሥራ ሂደቱ ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስላጋጠሙ ችግሮችና ስለተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች እንዲሁም የማሻሻያ አስተያየቶችን ያካተተ ሪፖርት በየጊዜው ለሚመለከተው ሪፖርት ያቀርባል፤
-
የሥራ ሂደቱ ስራዎች በተቀመጠላቸው የሰዓት ልኬት (standard time) መሠረት መከናወናቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤
-
የማሰልጠን፣ የማብቃት እና ተተኪ የማፍራት (coaching and monitoring) ስራዎችን ያከናውናል፤
-
በተጨማሪም የሥራ ሂደቱ የሚጠይቃቸውን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራት ያከናውናል፣ ያስፈéማል፣ ያስተባብራል::