ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኞች የበዓል ማክበሪያ ግብዓቶች ድጋፍ አደረገ

 

ድርጅቱ ማህበራዊ ኃላፊነት በመወጣት በኩል የሚያከናውናቸውን ተግባራት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ፡፡

የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኞች 2015. የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ የበዓሉ ማክበሪያ የሚውለውን ዶሮ፣ እንቁላልና የምግብ ዘይት ጳጉሜን 03 ቀን 2014 . ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር የሴቶች፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ /ቤት አስተባባሪነት ድጋፍ እንዲደረግላቸው ተለይተው ለቀረቡ 100 በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኞች ለእያንዳንዳቸው 1 ዶሮ 12 እንቁላል እና ባለ 1 ሊትር የምግብ ዘይት ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ድጋፉን የድርጅቱ ህዝብ ግንኙነትና ማህበራዊ ጉዳዮች /ቤት ኃላፊ የሁኑት አቶ ዳንኤል ኃይለ አስረክበዋል፡፡

አቶ ዳንኤል ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት ድርጅቱ ከመደበኛው ሥራው ባሻገር በማህበራዊ ኃላፊነት ሥራዎችም የነቃ ተሳትፎ እያደረገ እንደሆነና ይህንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡