ተግባርና ኃላፊነት
-
የሥራ ሂደቱን ሥራ ያቅዳል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ይቆጣጠራል
-
ድርጅት አቀፍ ሪስክ ፍተሻ እንዲካሄድና የውስጥ ቁጥጥር እንደሚሹ በፍተሻ የተለዩ ጉዳዮችን ከተቀዳሚነት (priority) እና ከሚጠይቁት የትኩረት ደረጃ አንጻር እንዲለዩ ያደርጋል፣ ተፈጻሚ ያደርጋል፤ የሥራ ሂደቱን የሰው ኃይል አስተባብሮ የኦዲት ዕቅድ ያዘጋጃል የኦዲት ምርመራና ክትትል ሥራዎችን በዚሁ መሰረት ያስፈጽማል፤
-
የሙያና የአሰራር ነጻነት ያለው የውስጥ ኦዲት ምርመራና ግምገማ እንዲደረግ እና ድርጅቱ የሥራ አፈጻጸም ጥራትና ደረጃውን ለመለካት የዘረጋው አጠቃላይ የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት በተግባር ሲፈተሽ በቂና ውጤታማ ስለመሆኑ ተገቢው ግብረመልስ እንዲሰጥ ያደርጋል፤
-
በየጊዜው ድርጅት አቀፍ የሪስክ ፍተሻ እንዲካሄድ፣ የድርጅቱን ግቦች ለማሳካት የሚደረገውን ጥረትና ሂደት የሚያደናቅፉ ሁኔታዎች (potential risks) እንዲለዩና በሚመለከታቸው የድርጅቱ የስራ አመራር አባላት ተገቢው ትኩረት እንዲሰጥባቸው ያደርጋል፣ ከዚህ አንጻር በስራ አመራሩ ተገቢው የመከላከል እርምጃ መወሰዱን ያረጋግጣል፤
-
በተያዘው የኦዲት ዕቅድ መሰረት የድርጅቱ ሪስክ ማኔጅመንት፣ የውስጥ ቁጥጥር እና አመራር (governance) ውጤታማ ስለመሆኑ ክትትልና ግምገማ በማካሄድና ለሥራ አመራሩ ተገቢ የማሻሻያ ሀሳቦችን በመስጠት የሥራ ሂደቱ ለድርጅታዊ ዓላማ መሳካት የሚያግዝ አገልግሎት እንዲሰጥ ያደርጋል፤
-
የኦዲት ምርመራ የሚካሄድባቸውን ሰነዶችና መረጃዎች ምስጢራዊነትና ደህንነት ያስጠብቃል፤
-
የኦዲት ምርመራ ውጤቶችን ለሚመለከታቸው የድርጅቱ የሥራ መሪዎችና ለኦዲት ኮሚቴ እያቀረበ ተገቢው የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፤የተወሰዱት እርምጃዎች የታለመላቸውን ውጤት ማስገኘታቸውን ተከታትሎ ያረጋግጣል፤
-
የውስጥ ቁጥጥር ስርዓቱ የድርጅቱ የስራ ሂደቶች የየፊናቸውን ተልዕኮና ግብ እያሳኩ ስለመሆናቸው፣ የድርጅቱን የፋይናንስ ሪፖርቶች ተዓማኒነትና አግባብነት ለአላቸው ህግና ደንቦች ያላቸውን ተገዥነት ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን ያረጋግጣል፤
-
በድርጅቱ አጠቃላይ አስተዳደራዊ (governance) ጉዳዮች ላይ የኦዲት ግምገማ በማድረግ በተለያዩ የድርጅቱ የስራ አመራር ደረጃዎች የተቀመጡ ግቦች (objectives) በተዋረድም ሆነ ወደጎን የሚጣጣሙና የሚደጋገፉ (aligned & congruent) መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
-
የድርጅቱ የሀብት አጠቃቀም (resource utilization) ወጪ ቆጣቢ፣ አዋጪና ውጤታማ ስለመሆኑ ወይም ስለአለመሆኑ ግብረ መልስ ይሰጣል፤
-
የንብረት መቆጣጠሪያና መከታተያ ስርዓቱ ብቃት እንዲፈተሽና የቆጠራ ውጤቶችና የንብረት ክትትልና ቁጥጥር መረጃዎች የሚጣጣሙ መሆናቸው ወይም አለመሆናቸው እንዲረጋገጥ ያደርጋል፤
-
የድርጅቱ የውስጥ ቁጥጥር ስርዓቶች የዕቅዶችን፣ የስራ ትዕዛዞችን፣ የመመሪያዎችንና አሰራሮችን ተፈጻሚነት (compliance) ለማረጋገጥ በቂ ስለመሆናቸው በኦዲት ምርመራ እንዲረጋገጥ ያደርጋል፤
-
ለብክነት፣ ምዝበራና ማጭበርበር ቀዳዳ በሚከፍቱ አሰራሮችና ስርዓቶች ላይ ተገቢ የማሻሻያና ማስተካከያ ሀሳቦችን እያቀረበና እያስጸደቀ ተፈጻሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
-
በሂሳብ አያያዝና በአሰራር ጉዳዮች ላይ አስተማማኝ የውስጥ ቁጥጥር ለማድረግ በሚያስችሉ ስልቶች ወይም ስርዓቶች አቀራረጽና አጠቃቀም የሥራ ሂደቶችን ያማክራል፤
-
በኦዲት ምርመራ በተገኙ የአሰራር ጉድለቶችና ብልሽቶች ላይ ተገቢው የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ለሚመለከተው የሥራ መሪ ወይም የስራ ሂደት ጥቆማ ወይም ሪፖርት ያቀርባል፤
-
የአዳዲስ ስርዓቶችና የስራ ሂደቶች ዝርጋታ ሲደረግ በቂና አስተማማኝ የውስጥ ቁጥጥር ስልቶችም ስለሚካተቱበት ሁኔታ የሥራ ሂደቱ ለስራ አመራሩ ተገቢውን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሰጥ ያደርጋል፤
-
በኦዲት ኮሚቴ ወይም በድርጅቱ ስራ አመራር ትዕዛዝና ጥያቄ መሰረት መደበኛ ያልሆኑ የፍተሻ፣ የማጣራትና የምርመራ ስራዎች እንዲከናወኑ ያደርጋል፤
-
በመንግስት የወጡ አዋጆችና ደንቦች እንዲሁም በሥራ አመራር ቦርድ የሚሰጡ መመሪያዎች በትክክል በሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤
-
ለውጭ ኦዲተሮች አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል፣
-
በሥሩ ያሉ የኦዲት ባለሙያዎችን የሥራ አፈጻጸም ይገመግማል፣
-
የሥራ ሂደቱን መደበኛና ልዩ ሪፖርቶች አዘጋጅቶ ያቀርባል፣
-
በኦዲተሮች የሚቀርበውን የኦዲት ሪፖርት ይመረምራል፣ ትክክለኛነቱን ያረጋግጣል፤
-
የድርጅቱ የኦዲት አገልግሎት የሥራ ሂደት ለድርጅቱ ዓላማ ግብ መምታት ተጨማሪ እሴት መፍጠሩን ያረጋግጣል፤
-
የኦዲት የናሙና መረጣን ያፀድቃል፤
-
የኦዲት የመለያ’ የትግበራ እና የሪፖርቲንግ ደረጃዎች (standards) ዓለም አቀፋዊነት ይዘት እንዲጠብቁ ያደርጋል፤
-
ኦዲተሮች በየኘሮግራሞቻቸው መሠረት መስራታቸውን ያረጋግጣል፣ የሥራ እንቅስቃሴያቸውን ያስተባብራል፤
-
በማኔጅመንት ስብሰባ ላይ የሥራ ሂደቱን ወክሎ ይሣተፋል፣ በኦዲት ጉዳዮች ዙሪያ የድርጅቱን ሥራ አመራር እና የሥራ አመራር ቦርድ ያማክራል፤
-
ለሥራ አመራር ቦርድና ለማኔጅመንቱ በቀረቡ የኦዲት ሪፖርቶችና በተደረጉ የግምገማ አስተያየቶችና ውሳኔዎች መሰረት የዕርምት እርምጃዎች መወሰዳቸውን ይከታተላል፣ ወቅታዊ እርምጃ ባልተወሰደባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ማኔጅመንቱን ያሳስባል፣ እንደአስፈላጊነቱም ለኦዲት ኮሚቴ ሪፖርት ያቀርባል፤
-
የሂደቱ ስራዎች በተቀመጠላቸው የሰዓት ልኬት (standard time) መሠረት መከናወናቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤
-
የማሰልጠን፣ የማብቃት እና ተተኪ የማፍራት (coaching and monitoring) ስራዎችን ያከናውናል፤
-
በተጨማሪም ከሥራ አመራር ቦርድ የሚታዘዙትን የሥራ ሂደቱ ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራት ያከናውናል፣ ያስፈጽማል፡፡