Ethics and Anti Corruption

ዓላማ

የድርጅቱ ፖሊሲዎች መመሪያዎች እና የመንግስት አዋጆች ፖሊሲዎችና መመሪያዎች በሚያስቀምጡት አቅጣጫ ብቻ ከድርጅቱ ሰራተኞችና ኃላፊዎች የሚመጡ ጥቆማዎችና ቅሬታዎችን ባግባቡ በማጣራት ሥነ ምግባር የሰፈነበት የሥራ አከባቢና ሙስናና ብልሹ አሰራር እንዲወገድ ማድረግ፣

ዋና ዋና ተግባራት

    • ሙስናና ብልሹአሰራርን ለማስወገድ ዕቅድ ይነድፋል::
    • ከተመሳሳይ ድርጅቶች የምርጥ ተሞክሮችን በመቅሰም ለድርጅቱ እንዲስማማ በማድረግ ይቀርፃል፡
    • ለድርጅቱ ሰራተኞችና ሥራ መሪዎች መልካም ሥነ ምግባርን የሚያዳብር ሥልጠና ይሰጣል፡፡
    • ሙስናን የሚጸየፍ ትውልድ ለመፍጠር ብርቱ ጥረት ያደርጋል፤

ዝርዝር ተግባራት

  • የፀረ-ሙስና ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች፣ የመልካም ሥነ ምግባር፣ የሙስና አስከፊ ገጽታዎችና ጎጂነት ግንዛቤ እንዲዳብር ያደርጋል፤

  • የድርጅቱን የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የሥነ ምግባር መመሪያ አግባብነት ካላቸው የሥራ ክፍሎች ጋር በመሆን ያዘጋጃል፤

  • ለድርጅቱ ሰራተኞችና የሥራ መሪዎች ተከታታይ የሥነ ምግባር ሥልጠናዎች ያዘጋጃል፤ ከሚመለከተው አካል/ክፍል ጋር በመሆን ይሰጣል፣ ያሰጣል፣

  • ለሙስናና ለብልሹ አሰራር ቀዳዳ የሚከፍቱ አሠራሮች እንዲስተካከሉ ያደርጋል፤

  • ለስትራቴጂክ ዕቅድ ዝግጅት የተሟላ የክፍሉን መረጃ/ግብዓት ይሰጣል፤

  • በድርጅቱ ውስጥ ሥነምግባር እንዲዳብር፤ የኃላፊነት ስሜት እንዲጎለብትና ሙስናን ለማጋለጥ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ያበረታታል፤ ጥቆማዎችን ተቀብሎ በማጣራት ተገቢውን ይፈጽማል፤ ያስፈጽማል፤

  • የድርጅቱ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የፀረ-ሙስና ፖሊሲዎች፣ የፀረ-ሙስና ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች፣ የመልካም ሥነ ምግባር፣ የሙስና አስከፊ ገጽታዎችና ጎጂነት ግንዛቤ እንዲያገኙ ያደርጋል፤

  • የፀረ ሙስና ፖሊሲዎች፣ የፀረ ሙስና ህጎች፣ የድርጅቱ ደንቦችና መመሪያዎች መከበራቸውን ይከታተላል፣ ስለአፈጻጸማቸውም የድርጅቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ያማክራል፤

  • በድርጅቱ ለሙስናና ለብልሹ አሰራር ቀዳዳ የሚከፍቱ አሠራሮ እንዲስተካከሉ ለጥናት የሚሆኑ መነሻ ሀሳቦችን በማመንጨት ለኮሚሽኑ ማሳወቅ፣ ይህንኑ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንዲያውቁት ይደረጋል፤ በራሱ ወይም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ጥናት በማድረግ አማራጭ ሀሳቦን ለዋና ሥራ አስፈጻሚ ያቀርባል፣ ሲወሰንም ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤

  • ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ጋር በመሆን የአስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ለደንበኛ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ለመስጠት በሚያስችል መልክ እንዲሻሻል የድርጅቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማማከር፣ በድርጅቱ አገልግሎት አሰጣጥ መድልዎ እንዳይፈጸም ይከታተላል፣ መድልዎ ተፈጽሞ ሲገኝ ለድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሪፖርት ያደርጋል፤

  • የሙስና ወንጀል ስለፈጸሙ ራሱ ጥርጣሬ ሲኖረው ወይም ከሌሎች ወገኖች የሚቀርቡ ጥቆማዎች ካሉ ተቀብሎ ይመዘግባል፣ ለኮሚሽኑ ሪፖርት ያደርጋል፣ ይህንኑ ለድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ያሳውቃል፤ ጉዳዩ የደረሰበትን ሁኔታ ይከታተላል፤

  • በድርጅቱ ውስጥ ስነ ምግባር እንዲዳብር፣ የኃላፊነት ስሜት እንዲጎለብትና ሙስናን ለማጋለጥ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለማበረታታት ሠራተኛውን ከቂም በቀል እርምጃ ለመከላከል የሚያስችል ሥርዓት በሚዘረጋበት ሁኔታ ላይ የድርጅቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ያማክራል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፤

  • የሥነ ምግባር ጥሰቶችን የሚመለከቱ ጥቆማዎችን ተቀብሎ በድርጅቱ ደንብና መመሪ መሠረት በማጣራት በቀጣይነት መደረግ ስለሚገባው ምርመራና መወሰድ ስለሚገባው እርምጃ የውሳኔ ሀሳብ ለድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ያቀርባል፤ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤ ስለአፈጻጸሙ ለዋና ሥራ አስፈጻሚ ሪፖርት ያቀርባል፤

  • የሠራተኛን ቅጥር፣ ዕድገት፣ ዝውውር ወይም ሥልጠና የዕቃ ወይም የአገልግሎት ግዥን ወይም የማንኛውንም ውል በሚመለከት ደንብና መመሪ ሲጣስ ለድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማስተካከያ እንዲደረግ ከአስተያየት ጋር ሪፖርት ያደርጋል፤ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፤

  • ሠራተኛው የሙስና ወንጀልና ከመልካም ሥነ ምግባር ተቃራኒ የሆኑ ድርጊቶችን በማጋለጡ ማንኛውም ተፅዕኖ እንዳይደርስበት ክትትል ያደርጋል፤ ተፅዕኖ ያደረገ ወይም የቀጣ ወይም ተፅዕኖ ለማድረግ ወይም ለመቅጣት የሞከረ ካለ ያጣራል ከተጨባጭ ማስረጃ ጋር ድርጊቱን ለድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሪፖርት ማድረግ፣ ስለሚወሰድበት ርምጃ ይከታተላል፣ ተፅዕኖ አድራጊ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከሆነ ጉዳዩን ለኮሚሽኑ ወይም ለሚመለከተው የምርመራ አካል ያሳውቃል፤

  • በድርጅቱ የሥነ ምግባር ጉዳዮች ወይም ችግሮች ላይ ሠራተኛው ወቅታዊ ውይይት እንዲያደርግ ለድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በጽሁፍ ያሳስባል፤

  • በራሱ ወይም በውጭ ወይም በውስጥ ኦተሮ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ወይም እንዲስተካከሉ ሪፖርት በቀረበባቸው ጉዳዮች ላይ ስለተወሰደው እርምጃ ሪፖርቶችና ውሳኔ የተሰጠባቸው ጉዮች ላይ ክትትል በማድረግ ለድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንዲሁም በግልባጭ ለመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴርና ለኮሚሽኑ ያሳውቃል፤

  • በህግ ወይም በመመሪያ በሚመጣ መስፈርት መሠረት ሙስናን ወይም ብልሹ አሰራርን በመዋጋት ግንባር ቀደም የሆነ አርአያነት ያላቸውን የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ዝርዝር መረጃ መዝግቦ መያዝና ሲያስፈልግና ሲጠየቅ መረጃውን ለዋና ሥራ አስፈጻሚ በማሳወቅ ለኮሚሽኑ ይሠጣል፤

  • ሥነ ምግባርን በማስፈንና ሙስናንና ብልሹ አሠራርን በመዋጋት ረገድ በድርጅቱ ውስጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ያቀናጃል፤

  • በየበጀት ዓመቱ ስለሚከናወኑ ተግባራት እቅድ፣ መርሃ ግብርና በጀት ማዘጋጀትና ለድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚና ለኮሚሽኑ ያቀርባል፣ ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤

  • ከቅርብ የሥራ መሪው በሚሰጠው አጠቃላይ የሥራ ትዕዛዝ መሰረትና ሌሎች ተዛማጅ ተግባራት ያከናውናል፡፡