ዓላማ
የድርጅቱን ስትራቴጂክ ዕቅድ ዝግጅትና ትግበራ ላይ ተሳትፎ ማድርግ፤ የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ የጥራት ሥራ አመራርና የአሠራር ማሻሻያ ፖሊሲዎችንና መመሪያዎችን በማዘጋጀትና ተግባራዊ እንዲሆን ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፤ ለምርት ጥራት መንስዔ የሆኑ ችግሮችን በማጥናት የመፍተሄ ሃሳብ በማቅረብ የደንበኛ ፍላጎት እንዲሟላ ማድርግ፤
ዋና ዋና ተግባራት
-
በድርጅቱ ስትራቴጂክ ዕቅድ ዝግጅትና ትግበራ ላይ ግብዓት በመስጠትና በማስፈጸም የነቃ ተሳትፎ ያደርጋል፤
-
በድርጅቱ በሥራ ላይ እንዲውል የመረጃ ማሰባሰቢያና ማቀነባበሪያ ሲስተም /ኢንተግሬትድ ማኔጅመንት ኢንፎርሜiን ሲስተም/ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
-
የኮምፒውተራይዝድ ኢንፎርሜሽን ሲስተም ዲዛይን ቀረጻ፣ ዳታቤዝ ምስረታና ማኔጅመንት’ የኔትወርክ አደረጃጀት’ የፕሮግራምና ሲስተም ሥራዎችን፣ የጥገናና ድጋፍ አገልግሎቶችን፣ የዌብሳይት አስተዳደር ሥራዎችን በበላይነት ይመራል፤
-
የድርጅቱን የአሰራር ዘዴና የአገልግሎት አሰጣጥ እየተከታተለና እየገመገመ ነባር አሰራሮች የሚሻሻሉበትን፣ ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥ የሚጎለብትበትን ጥናት በማስጠናት ድርጅቱ ተወዳዳሪና ተጠቃሚ እንዲሆን ያደርጋል፤
-
ከመንግስት እንዲተገበሩ የሚላኩ የአሠራር ሥርዓት ማሻሻያ መርሃ-ግብሮችን ወይም የለውጥ መሣሪያዎችን ይመራል፤ ያሉበትን ደረጃ እየገመገመ ሪፖርት ያቀርባል፤
-
የድርጅቱን የጥራት ሥራ አመራር መርሆዎች መተግበር አዳዲስ የጥራት ሥራ አመራር ዘዴዎችን ማጥናትና መተግበር፣
-
የሥራ ሂደቱን በመምራት፣ በማስተባበር፣ በማሠልጠንና በማብቃት የቡድን ሥራን ማዳበርና ባህል በማድረግ ውጤታማ ሥራ እንዲሠራ ማድረግ፣
-
የሥራ ሂደቱን ዕቅድ ማዘጋጀት ማፀደቅና ማስፈፀም፤