ተግባርና ኃላፊነት
-
የሥራ ሂደቱን ሥራ ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ የዘርፉን የሠው ኃይል ፍላጎት ያሟላል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል፣ይቆጣጠራል&
-
የውጭ ቅኝት፣ የላቀ ተሞክሮ ቅኝት (benchmarking)፣ ስትራቴጂያዊ ዕቅድና የፕሮጀክት ሰነድ ዝግጅት፣ የምርትና ሽያጭ ዕቅድ አፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ሪፖርት ዝግጅት፣ በህትመት መሣሪያዎች መቆም ምክንያት የተጓደለውን የምርት ዋጋ ሪፖርት ዝግጅት፣ የድርጅቱን የአቅም አጠቃቀም፣ የሠራተኛውን የነፍስ ወከፍ ምርታማነት ስሌት እና የድርጅቱን የሥራ ቅበላና ክትትል በአጠቃላይ የድርጅቱን የዕቅድ ክትትልና ግምገማ ሪፖርት ዝግጅት ተግባራት ያስተባብራል፣ ይመራል፣ይቆጣጠራል&
-
ከሚመለከታቸው የሥራ ሂደቶች ጋር በመተባበር ልዩ ልዩ አዳዲስ የፕሮጀክት ሀሳቦችን ያመነጫል፣ ፕሮፋይል ያዘጋጃል፣ ተዘጋጅተው የቀረቡ ፕሮፋይሎችን በመመርመር አስተያየት ይሰጣል፣ የፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ከተቀመጠላቸው ዕቅድ አንጻር ይከታተላል፣ ይገመግማል፤
-
ልዩ ልዩ የማስፋፊያና የመተኪያ የኢንቨስትመንት አማራጭ ሀሳቦችን ያቀርባል፣ ይገመግማል፣ ሲçድቁ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፤
-
አስፈላጊ መረጃዎች እንዲሰባሰቡ በማድረግ የድርጅቱን ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ሌሎች የሥራ ሂደቶችን አስተባብሮ ያዘጋጃል፤
-
የመሪ ዕቅድ አፈፃፀም መርሃ ግብር (action plan) በማዘጋጀት ለሥራ ሂደቶች ያሰራጫል፣ክትትልና ግምገማ ያደርጋል፤
-
የዕቅድ አፈፃፀሞችን በአፈፃፀም መለኪያዎች በመገምገም የእርምትና የማስተካከያ ዕርምጃዎች እንዲወሰዱ ለሚመለከተው ሪፖርት ያቀርባል&
-
ለድርጅቱ ሥራ አመራር፣ ለሥራ አመራር ቦርድ፣ ለመንግስት የልማት ድርጅቶች ወዘተ የሚቀርቡ ሪፖርቶች በሚፈለገው ጊዜ ተዘጋጅተው እንዲቀርቡ ያደርጋል፤
-
የድርጅቱ የወደፊት መልካምና መጥፎ አጋጣሚዎችን በመለየት በቀጣይ መወሰድ የሚገባቸውን የመፍትሄ ሀሳቦች ያቀርባል&
-
የድርጅቱን የአለፉት ዓመታት የዕቅድና ክንውን መረጃ የሥራ አፈèçሙን አካሄድ (trend) በሚያሳዩ የተለያዩ የመረጃ አቀራረብ ስልቶች ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ ያደርጋል፤
-
የሂደቱ ስራዎች በተቀመጠላቸው የሰዓት ልኬት (standard time) መሠረት መከናወናቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤
-
የማሰልጠን፣ የማብቃት እና ተተኪ የማፍራት (coaching and monitoring) ስራዎችን ያከናውናል፤
-
የሥራ ሂደቱ የውስጥና የውጪ ደንበኞች መረጃ ሲፈልጉ የድርጅቱ አሰራር በሚፈቅደው መሰረት እንዲሰጡ ያደርጋል፤
-
የሥራ ሂደቱን ባለሙያዎች የሥራ አፈèçም ግምገማ ሞልቶ ያቀርባል፤
-
የሥራ ሂደቱን መደበኛና ልዩ ሪፖርቶች በወቅቱና በሚፈለገው የጥራት ደረጃ ተዘጋጅተው እንዲቀርቡ ያደርጋል፤
-
የሥራ ሂደቱን ሌሎች ተዛማጅ ተግባራት ያከናውናል፣ያስፈጽማል፡፡