Human Resource Management & General Service directorate

ተግባርና ኃላፊነት

  • የሥራ ሂደቱን ተግባራት ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል፣  ይቆጣጠራል፤

  • የድርጅቱ የሰው ሀብት ስልጠናና ልማት ተግባራት በወጣላቸው የአፈጻጸም     መርሃ ግብር መሰረት መፈጸማቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣ተኪ  የሚያስፈልጋቸው የሥራ መደቦች ተኪ እንዲዘጋጅላቸው ያደርጋል፤

  • የሥራ ሂደቱ ፖሊሲዎች፣ መመሪያዎች፣ ደንቦችና አሠራሮች እንዲቀረè፣ ወይም እንዳስፈላጊነቱ በሥራ ላይ ያሉት እንዲሻሻሉ ሀሳብ ያቀርባል፤

  • ለሥራ ሂደቱ የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችና ቁሳቁሶች በወቅቱ እንዲሟሉ ያደርጋል፣

  • የቅጥር፣ የዕድገትና የዲስፕሊን ኮሚቴዎችን እና ሌሎች የሥራ ሂደቱ ኮሚቴዎችን በሰብሳቢነት ይመራል፣ ያስፈጽማል፤

  • የሰራተኛ አስተዳደር፣ የሙያ ደህንነትና ጤንነት ሥራዎች በድርጅቱ ደንብና መመሪያ መሠረት መከናወናቸውን ያረጋግጣል፤

  • ከሠራተኛ ማህበር ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ተገቢውን መልስና ማብራሪያ በወቅቱ ይሰጣል፣ አስፈላጊም ሲሆን ውይይት በማካሄድ ለችግሮች መፍትሄ ይሰጣል፤

  • ከድርጅቱ ልዩ ልዩ የሥራ ሂደቶች የሚቀርበውን የሰው ሀብት ጥያቄ መርምሮ ከአስተያየት ጋር ለውሳኔ ያቀርባል፣ በራሱ የሚወሰኑትን ይወስናል፤

  • የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ፣ የድርጅቱ መመሪያዎች፣ ደንቦችና የሕብረት ስምምነት በአግባቡ ሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፤

  • የሰው ሀብት ጥያቄ (employment requisition) የሚቀርብባቸው ክፍት የሥራ መደቦች የድርጅቱን የአሠራር ስርዓት በመከተል መስፈርቶችን በሚያሟላ የሰው ኃይል እንደየአግባብነቱ በዝውውር፣ በዕድገት፣ በቅጥር እንዲሟሉ ያደርጋል፤

  • የድርጅቱ የሰው ኃይል የየወቅቱን የቴክኖሎጂ ዕድገትና የውድድር ሁኔታ መሠረት በማድረግ ተከታታይ የሥራ ላይ፣ የውስጥ እና የውጭ ስልጠና እንዲያገኝ ያደርጋል፤

  • የሠራተኞች የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በተያዘለት የጊዜ ገደብና የአፈጻጸም ስርዓት መሠረት መፈጸሙን ያረጋግጣል፤

  • በሠው †ይል ጉዳዮች ዙሪያ ከሌሎች የድርጅቱ የሥራ ሂደቶችና ከልዩ ልዩ ድርጅቶች ጋር የሥራ ግንኙነት ያደርጋል፤

  • ድርጅቱን በመወከል ከሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ከሠራተኛ ማሕበር ጋር የሕብረት ስምምነት ይደራደራል፤

  • የድርጅቱና የሠራተኛው ግንኙነት የሰመረ እንዲሆን አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል፤

  • የድርጅቱና የሠራተኛው መብትና ጥቅም በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ እና በድርጅቱ የህብረት ስምምነት መሠረት እንዲጠበቅ ያደርጋል፤

  • የድርጅቱን የሠው †ይል የክፍያ ስርዓትና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ከየወቅቱ የሠው †ይል ገበያ የክፍያ ስርዓትና ጥቅማጥቅሞች ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆን ያደርጋል፤

  • የሥራ ሂደቱን የሥራ ማስኬጃና ካፒታል በጀት ያዘጋጃል፣ ሲፈቀድ አጠቃቀሙን ይቆጣጠራል፤

  • የድርጅቱ ሪኮርዶችና የሠራተኛ የግል ማህደሮች በሚገባ መያዛቸውንና ተገቢውን አገልግሎት መስጠታቸውን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤

  • የሥራ ሂደቱ ስራዎች በተቀመጠላቸው የሰዓት ልኬት (standard time) መሠረት መከናወናቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤

  • የማሰልጠን፣ የማብቃት እና ተተኪ የማፍራት (coaching and monitoring) ስራዎችን ያከናውናል፤

  • በተጨማሪም ከቅርብ የሥራ መሪዉ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት የሥራ ሂደቱን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፣ ያስፈጽማል፡፡