ዓላማ

ስትራቴጂክ ዕቅዶች የማዘጋጀት፣ ዕቅድን ከበጀት ጋር አጣጥሞ የመያዝና የመፈፀም፣ የሥልጠና አቅም ማሳደግ፣ የሠልጣኝ ቅበላ አቅም ማሳደግ፣ደረጃውን የጠበቅ ሥልጠና እንዲሠጥ ማድረግ፣ የሥልጠና ማዕከሉን መልካም ስም መጠበቅ፣ ተደራሽነትን ማስፋት፣ ከሥሩ ያሉትን ባለሙያዎች በአግባቡ ማስተዳደር፣ መምራት፣ መቆጣጠር፣ መገምገም አጠቃላይ ኃላፊነት አለበት።

ዋና ዋና ተግባራት

  • የሥራ ሂደቱን ስትራቴጂክ ዕቅድና በጀት ያዘጋጃል፣
  • ከሥሩ ያሉ ሠራተኛችን ይመራል፣ ያስተባብራል፤
  • የዐሰራር ስርዓቱን ያሻሽላል፣ ይለውጣል፤
  • የሥልጠና አቅም ያሳድጋል፣ የቅበላ አቅም ያሳድጋል፣ ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር ማዕከሉ እንዲሂድ ያደርጋል፡፡

ዝርዝር ተግባራት

  • የዳይሬክቶሬቱን ተግባራት ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ይቆጣጠራል፣
  • የዳይቴክቶሬቱን የአፈጻጸም መመሪያዎች፣ አሠራሮች ይቀርጻል እንደአስፈላጊነቱ በሥራ ላይ ያለው እንዲሻሻል ሀሳብ ያቀርባል፣
  • የአካዳሚ የአፈጻጸም መመሪያ መሠረት በማዕከሉ ለመሰልጠን የሚፈልጉ የውጭና የውስጥ አመልካቾችን ተቀብሎ እንዲሰለጥኑ ያደርጋል፣
  • በአካዳሚው የተመረቁም ሆነ በውጭ ተቋማት ሰልጥነው የብቃት ማረጋገጫ ላለፉት ሰልጣኞች በማዕከሉ የአፈጻጸም መመሪያ መሠረት ደንበኞች ጥያቄ ሲያቀርቡ ተጨማሪ የስልጠና ኘሮግራም ያዘጋጃል፣
  • የአካዳሚ የስልጠና ተግባራት በወጣላቸው የአፈጻጸም መርሐ ግብር መሠረት መፈፀሙን ይከታተላል፣
  • ካለፉት ዓመታት የሰልጣች ዝርዝር መረጃ በመነሳት የቀጣይ ዓመት የስልጠና ፍላጐቶችን እቅድ በማዘጋጀት የአፈጻጸም ክትትል ያደርጋል፣
  • የየትምህርት ዘርፉ ኃላፊዎች ጋር በጋራም ሆነ በግል ይወያያል አስፈላጊ ሲሆን የመማር ማስተማሩን ሒደት ለማሻሻል የሚያስችሉ ሀሳቦችን አቅርቦ ተፈጻሚነቱን ይከታተላል፣
  • በሕትመት ስልጠና ዙሪያ ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ አገር ግንኙነት ይፈጥራል፣ የልምድ ልውውጥ ያደረጋል፣ ተቋሙን ያስተዋውቃል፣ ዓለም አቀፍ ግንኙነት እንዲኖረው ያደርጋል፣
  • በአካዳሚው የምርምርና የስርፀት ተግባራቶችን ለማካሄድ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች እንዲኖሩ ተገቢውን ጥረት ያደርጋል፣
  • የሕትመት ዘርፉን ትምህርትና ስልጠና ሊያጐለብቱ የሚችሉ ጥኖቶች፣ ወርክሾፖች፣ ሴሚናሮች፣ ተዘጋጅተው የዕውቀት ሽግግር እንዲደረግ ያስተባብራል፣
  • ከድርጅቱ ዳይሬክቶሬቶች ለሰው ሀብት ስራ አመራርና ልማት ዳይሬክቶሬት ቀርበው በስልጠና ማዕከሉ ስልጠና እንዲሰጥ በዋና ሥራ አስፈጻሚ የተወሰኑትን ተቀብሎ እንዲሰለጥኑ ያደርጋል፣
  • የአሰልጣኞችን ወቅታዊ አቋም ይገመግማል፣ ድክመት ሲያሳዩ አቅም ይፈጥራል፣ በማይሻሻሉት ላይ ተገቢውን እርምጃ እንዲወሰድ ያቀርባል፡
  • ድርጅቱን በመወከል ከሌሎች ተቋማት ጋር ግንኙነት ይፈጥራል፣ የተሞክሮ ልምድ ልውውጥ በማድረግ የተቋሙን አፈጻጸም ይፈትሻል፣ ያጠናክራል፣ አቅም ይፈጥራል፣ ተደራሽነቱን ያሰፋል፣
  • የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜያት የስልጠና ዕቅድ ያወጣል፣ አፈጻጸሙን ይገመግማል፣
  • የሰልጣኞች ቅበላ እቅድ፣ ምዝገባ/ የስልጠናና ትምህርት ውጤት ማጠናቀርና ትምህርታቸውን ተከታትለው ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የስልጠናና የትምህርት ማስረጃ ያዘጋጃል፣
  • የተቋሙን የሰው ኃይል በመዋቅር በተፈቀደለት ዓይነትና ብዛት መሠረት እንደአግባብነታቸው በማየት እንዲሟሉ ያደርጋል፣
  • የተቋሙን ገቢና ወጭ ሂሳብ ከሚመለከተው ዳይሬክቶሬት ጋር በመገናኘት በየጊዜው ሪፖርት እንዲቀርብለት ክትትል ያደርጋል፣
  • የተቋሙ የስልጠና ሂደት የሰመረ እንዲሆን አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል፣ በስልጠና ማዕከሉ የሚገቡ ሰልጣኞችን ተቀብሎ የማሰልጠንና የማብቃት ስራዎችን ያከናውናል፣
  • የአካዳሚ አፈጻጸም ይገመግማል በግምገማው ውጤት መሠረት የማስተካከያ እርምጃዎችን ይወስዳል፣
  • በተጨማሪም ከቅርብ የሥራ ኃላፊው በሚሰጠው መመሪያ መሠረት የዳይሬክቶሬቱን እና ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራትን ያከናውናል፣ ያስፈጽማል፡፡