Security Printing Directorate

ዓላማ

የድርጅቱን ስትራቴጂክ ዕቅዶች ለማዘጋጀትና ማስፈፀም፣ የሥራ ሂደቱን በማሻሻልና በመለወጥ ምርታማነት የሚያድግበትን አሠራር መቀየስ፣ የማምረቻ መሣሪያዎች የዕቅድ ጥገና በጥራት ታቅደው ለሥራ ዝግጁ መሆናቸውን ማረጋገጥ ሠራተኞችን ለማብቃት፣ የውስጥ አቅሙን በማጎልበት የደንበኞችን ፍላጎት ለማርካት፣ አጠቃላይ የሥራ ሂደቱን ለማስተባበርና መምራት፤

ዋና ዋና ተግባራት

  •  የሥራ ሂደቱን ስትራቴጂክ ዕቅድ ያዘጋጃል
  •   ከፍተኛ የህትመት ሥራ ውሎችን ይፈራረማል
  •   የማምረቻ መሣሪያዎች የዕቅድ ጥገና በፍጥነትና በጥራት ለሥራ ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል።
  •   የአሠራር ሂደቱን በመፈተሽ ያሻሽላል/ይለውጣል፣ያበቃል፣ቡድኑን ይመራል/ያስተባብራል¿
  •    በዕቅድ ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ይሳተፋል፣ ግብዓት ይሰጣል፤

ዝርዝር ተግባራት

  • በድርጅቱ የስትራቴጂክ ዕቅድ አጠቃላይ ውሳኔ በሚሹ ጉዳዮች ላይ ይሣተፋል

  • የዋና ሥራ ሂደቱን ስትራቴጂክ ዕቅድ ያዘጋጃል

  • በሥራ ሂደቱ ላሉት ሠራተኞች የምክር አገልግሎት ይሠጣል፣ ያሰለጥናል፣ ያበቃል

  • በሚስጢራዊ ሕትመት የሚከናወኑ ሥራዎች ሚስጢራዊነታቸው ተጠብቆ ለአሰሪው እንዲደርሱ በመከታተል ያስፈጽማል

  • በሥራ ሂደቱ የሚገኙ ሠራተኞችን የሥራ አፈፃፀም ይገመግማል

  • የስራ ሂደቱን በመወከል በዳይሬክተሮች (ስራ አመራር) ኮሚቴ እና በሌሎች የተለያዩ ስብሰባዎች ላይ ይሳተፋል ፣የስራ አመራር ኮሚቴውን የአመራር ስራ አብሮ ይሰራል፤

  • የሥራ ሂደቱን በመወከል ከፍተኛ የህትመት ውሎችን/ስምምነቶችን ይፈራረማል

  • በሥሩ ያሉ ቡድኖች ዕቅድ እንዲያዘጋጁ ያደርጋል፣ ሥራዎች በዕቅድ መሠራታቸውን ይከታተላል፣ረቂቅ የዕቅድ ማጠቃለያ ማዘጋጀት፣

  • የጥገና ቡድን ቅድመ ጥገና ዝግጅት ዕቅድ መያዙን ያረጋግጣል፣ የጥገና ቡድንን ይመራል፣ ያስተባብራል¿

  • የአሰራር ስርዓቱን ያሻሽላል፣ እንደአስፈላጊነቱ ይለውጣል

  • የሥራ ሂደቱን ቡድኖች ያደራጃል፣ ሥራዎችን ያቅዳል፣ የዘርፉን የሠው ኃይል ፍላጎት ያሟላል፣ ሚዛናዊ የሥራ ድልድል ያደርጋል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል፤

  • በስሩ ያሉ ቡድኖች ዕቅዳቸውን አዘጋጅተው እንዲያቀርቡ ይከታተላል፣ ረቂቅ የዕቅድ ማጠቃለያ ያዘጋጃል፤

  • የማምረቻ መሳሪያዋች መሟላታቸውን፣ በወቅቱ መጠገናቸውን ይከታተላል፣ የማምረቻ መሳሪያዎችን የማጠናከሪያ፣ የመተኪያ እና የአዲስ ካፒታል በጀት ያስይዛል፣ የመሳሪያዎች ቴክኒካዊ መረጃዎችና የጥገና ሪከርዶች በአግባቡ እንዲያዙ ያደርጋል፤

  • የስራ ሂደቱን ስራ በሚመለከት ውሳኔ ማግኘት የሚገባቸውን ጉዳዮች ይወስናል፤ የስራ ሂደቱን የአፈፃፀም ወቅታዊ ሪፖርት ያዘጋጃል፤

  • በበጀት ዓመቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴ በምርት፣ በበጀት አጠቃቀም፣ በምርታማነት፣ የደንበኛን እርካታ ከማስጠበቅ አንፃር አፈጻጸሙን በመለካትና በመገምገም ሪፖርት ያዘጋጃል፤ከቡድኖች ለሚመጡ ችግሮች መፍትሄ ይሰጣል፤

  • በስሩ ባሉ ቡድኖች ስር ያሉ ንዑስ ቡድኖች የሕትመት ስራ እንዳይስተጓጐል፣ ሕትመት በተያዘለት ዕቅድ፣ የጥሬ ዕቃ ፍጆታ መጠንና የጥራት ደረጃ ማከናወን በሚያስችል መልኩ ተቀናጅተው እንዲንቀሳቀሱ ያደርጋል፤

  • የስራ ሂደቱ ስራዎች በስራ ሂደቱ ደንብና መመሪያ እና የአሰራር ዝርዝር መሰረት እንዲከናወኑ ያደርጋል፣ መከናወናቸውን ያረጋግጣል፤

  • በሰው ሃይል፣ በማሽን ጥገና፣ በጥሬ ዕቃ አቅርቦትና በአጠቃላይ በምርት ሃደት ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮች ከሚመለከታቸው የስራ ሂደት ባለቤቶችና የቡድን መሪዎች ጋር በመወያየት መፍትሄ ያፈላልጋል፤

  • ማንኛውም የደንበኛ ትዕዛዝ በጥራት ጉድለት ምክንያት ከደንበኛው ቅሬታ ሲያጋጥመው አስፈላጊውን ማስተካከያ ከማድረግ ባሻገር መንስዔያቸው እየተጠና ለወደፊቱ በድጋሚ እንዳይከሰቱ የመፍትሄ እርምጃ ይወስዳል፤

  • የሥራ ሂደቱ ስራዎች በተቀመጠላቸው የሰዓት ልኬት (standard time) መሠረት መከናወናቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤

  • የማሰልጠን፣ የማብቃት እና ተተኪ የማፍራት (coaching and monitoring) ስራዎችን ያከናውናል፤

  • ከሥራ ሂደቱ የውጭና የውስጥ ደንበኞች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች መፍትሄ በማፈላለግ ውሳኔ ይሠጣል/እንዲሰጥ ያደርጋል

  • በሥልጠና ሂደት አፈፃፀም ከሠው ሀብት አመራር ደጋፊ የሥራ ሂደት ጋር በመተባበር ይሠራል

  • የሥራ ሂደቱን እና የሥራ ሂደት ቡድኖችን ያማክራል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል

  • የአሰራር ስርዓቶችን ተግባራዊ ያደርጋል ተፈጻሚነታቸዉን ይከታተላል::

  • በተሠጠው የሥልጣን ውክልና መሠረት ከሥራ ሂደቱ ጋር ግንኙነት ካላቸው የተለያዩ አካላት ጋር የሥራ ግንኙነት ያደርጋል

  • ሥራዎች በዕቅዱ መሠረት መከናወናቸውን ተከታተሎ በመገምገም ወቅታዊ ሪፖርት ያቀርባል፣

  • ከዋና ስራ አስፈፃሚ እና ከምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ የሚሰጡትን ሌሎች ሥራዎች ይሠራል