ዓላማ
የድርጅቱን ስትራቴጂክ ዕቅዶች ለማዘጋጀትና ማስፈፀም፣ የሥራ ሂደቱን በማሻሻልና በመለወጥ ምርታማነት የሚያድግበትን አሠራር መቀየስ፣ የማምረቻ መሣሪያዎች የዕቅድ ጥገና በጥራት ታቅደው ለሥራ ዝግጁ መሆናቸውን ማረጋገጥ ሠራተኞችን ለማብቃት፣ የውስጥ አቅሙን በማጎልበት የደንበኞችን ፍላጎት ለማርካት፣ አጠቃላይ የሥራ ሂደቱን ለማስተባበርና መምራት፤
ዋና ዋና ተግባራት
- የሥራ ሂደቱን ስትራቴጂክ ዕቅድ ያዘጋጃል
- ከፍተኛ የህትመት ሥራ ውሎችን ይፈራረማል
- የአሠራር ሂደቱን በመፈተሽ ያሻሽላል/ይለውጣል፣ያበቃል፣ቡድኑን ይመራል/ያስተባብራል
ዝርዝር ተግባራት
-
በድርጅቱ የስትራቴጂክ ዕቅድ አጠቃላይ ውሳኔ በሚሹ ጉዳዮች ላይ ይሣተፋል
-
የዋና ሥራ ሂደቱን ስትራቴጂክ ዕቅድ ያዘጋጃል
-
በሥራ ሂደቱ ላሉት ሠራተኞች የምክር አገልግሎት ይሠጣል፣ ያሰለጥናል፣ ያበቃል
-
በሥራ ሂደቱ የሚገኙ ሠራተኞችን የሥራ አፈፃፀም ይገመግማል
-
የሥራ ሂደቱን በመወከል ከፍተኛ የህትመት ውሎችን/ስምምነቶችን ይፈራረማል
-
በሥሩ ያሉ ቡድኖች ዕቅድ እንዲያዘጋጁ ያደርጋል፣ ሥራዎች በዕቅድ መሠራታቸውን ይከታተላል፣ረቂቅ የዕቅድ ማጠቃለያ ማዘጋጀት፣
-
የአሰራር ስርዓቱን ያሻሽላል፣ እንደአስፈላጊነቱ ይለውጣል
-
ከሥራ ሂደቱ የውጭና የውስጥ ደንበኞች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች መፍትሄ በማፈላለግ ውሳኔ ይሠጣል/እንዲሰጥ ያደርጋል
-
በሥልጠና ሂደት አፈጻፀም ከሠው ሀብት አመራር ደጋፊ የሥራ ሂደት ጋር በመተባበር ይሠራል
-
የሥራ ሂደቱን እና የሥራ ሂደት ቡድኖችን ያማክራል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል
-
በተሰጠው የሥልጣን ውክልና መሠረት ከሥራ ሂደቱ ጋር ግንኙነት ካላቸው የተለያዩ አካላት ጋር የሥራ ግንኙነት ያደርጋል
-
ሥራዎች በዕቅዱ መሠረት መከናወናቸውን ተከታተሎ በመገምገም ወቅታዊ ሪፖርት ያቀርባል፣
-
የአሰራር ስርዓቱን ተግባራዊ ያደርጋል ተፈጻሚነታቸዉን ይከታተላል::
-
ከዋና ስራ አስፈፃሚ እና ከምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ የሚሰጡትን ሌሎች ሥራዎች ይሠራል