መረጃ

በድርጅታችን የስነ ምግባር መከታተያ ክፍል ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ የተቋቋመ ሲሆን የፌደራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አንድ ቅርጫፍ ሆኖ የሚሰራ ዳይሬክቶሬት ነው፡፡ ዳይሬክቶሬቱም የሚያከናውናቸውም ተግባራት በሶስት ዋና ዋና ተግባራት የተከፈሉ ናቸው፡፡

  1. የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ትምህርትና ስልጠና መስጠት
  2. የሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የአሰራር ስርዓት ጥናት ማከናወን
  3. ከተለያዩ የድርጅቱ የውጪ እና የውስጥ ደንበኞች የሚቀርቡ የሙስና እና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ጥቆማ መቀበልና ማጣራት እንዲሁም ችግሩ ከአቅም በላይ ከሆነ

ለፌ/ስ/ም/መ/ፀ/ሙ/ኮሚሽን፣ ለፌደራል ፖሊስ የሙስና ወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት እና ለጠቅላይ አቃቤ ህግ ጥቆማውን በማቅረብ እንዲመረመር ማድረግ ነው፡፡

በመሆኑም የድርጅታችን የውጪ እና የውስጥ ደንበኞች በድርጅቱ ውስጥ አሉ የምትሉትን የሙስና እና የብልሹ አሰራር ጥቆማዎች ካሉ በአዲሱ ህንጻ 2ኛ ፎቅ የስነ ምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ፣ በፅፉፍ እና ከታች በተገለጹት የስልክ ቁጥሮች በመደወል ጥቆማዎችን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  • 0111551857 የውስጥ መስመር 357
  • 0912845145

የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት