Deputy Chief Executive Office Resource Management Sector

 

  • Human Resource management and Development Directorate

  • Finance Directorate

  • Procurement and Property Administration Directorate

ዓላማ

የድርጅቱ የአጭር፣ የመካከለኛና፣ የረዥም ጊዜ ዕቅድ ዝግጅት ላይ ይሳተፋል፣ ሲፈቀድም በሥሩ የሚገኙ የሥራ ሂደቶች በማስተባበር ተግባር ላይ እንዲውል ያደርጋል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤ የዋናው የስራ ሂደትን በሰው ሃይል፣ በጥሬ ዕቃና በፋይናንስ አቅርቦት በመደገፍ የምርት ሥራዎች ሳይስተጓጎሉ እንዲቀጥሉ ያደርጋል፤

 

ዋና ዋና ተግባራት

  • በድርጅቱ ስትራቴጂክ ዕቅድ ዝግጅት ላይ ይሳተፋል፤ ሲፈቀድም በዘርፉ የሚገኙ የሥራ ሂደቶችን በማስተባበር ተግባራዊ እንዲሆን ያድርጋል፤

  • በድርጅቱ ሥራ ላይ የሰው ሃይል፣ የፋይናንስና የጥሬ ዕቃ ዕጥረት እንዳይከሰት ቅድመ ዝግጅት በማድርግ የስራ መስተጓጎልን ይከላከላል፤

  • በዘርፉ የሚገኙ የሥራ ሂደቶችን የሰው ሀብት ይመራል፤ ያስተባብራል፤ አፈፃፀማቸውን ይገመግማል፤

  • የዘርፉን ሥራ ሂደቶች በማስተባበር የዘርፉንና በሥሩ ያሉ የስራ ሂደቶችን ዕቅድ በማዘጋጀት ሲፈቀድም ተፈጻሚ  ይገመግማል፤