የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 029/19

ድርጅታችን ዋናው መስሪያ ቤት የነባሩ ህንፃ 1ኛ እና 2ኛ ፎቅ ስራ ክፍል ወለል በኢፖክሲ የወለል ንጣፍ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች እንዲሁም ደረጃቸው GC 5 ወይም BC 4 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮች የጨረታ ሰነዱን በሲዲ በድርጅቱ አዲሱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 500.00 ከፍለው በመግዛት በድርጅቱ 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የፋይናንሻይልና የቴክኒካል የመጫረቻ ሠነዶቻቸውን በተለያየ ኢንቨሎኘ በማድረግ ማቅረብና ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ  አለባቸው፡፡ ጨረታው ህዳር 8/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰአት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የፋይናንሸያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ሰነድ ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡