15ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ተከበረ

ጥቅምት 07 ቀን 2015 ዓ.ም የተከበረው የብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን የብዝሃነታችን መገለጫ የሉዓላዊነታችን ምሰሶ ነው” በሚል መሪ ቃል ሲሆን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሽታሁን ዋለን ጨምሮ፣ የማኔጅመንት አባላት፣ ከየስራ ክፍሉ የተውጣጡ ሠራተኞች እና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በተገኙበት ተከብሯል፡፡

በዓሉ የኢትዮጵያን ህዝብ መዝሙር በመዘመርና ሰንደቅ ዓላማን በመስቀል ስነ-ስርዓት በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲከበር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተወሰነው መሰረት በተመሳሳይ ሰዓት ከረፋዱ 4፡30 ላይ ተከብሯል፡፡