ድርጅታችን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡-
በጨረታ አንድ (ሎት 1) ፡- ለሁለት አመት የሚቆይ የመነፅር ስራ አገልግሎት ግዥ፣
በጨረታ ሁለት (ሎት 2) ፡- ለሁለት አመት የሚቆይ የእሳት ማጥፊያ መሳሪያዎች ፍተሻ፣ ሙሌትና የመለዋወጫ አቅርቦት አገልግሎት ግዥ፣
በጨረታ ሶስት (ሎት 3) ፡- ካርቦን (HAND CARBON) ብዛት 150 ፓኬት ግዥ፣
ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲስ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 300.00 ከፍለው በመግዛት ፋይናንሺያል የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
ጨረታው ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰአት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የፋይናንሸያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡