
ዓላማ
ድርጅቱ ሥራውን በተመለከተና በማንኛውም ጊዜ የሚፈጽማቸውን ውሎች፣ስምምነቶችን ማማከር፣ ድርጅቱ በማንኛውም ጉዳይ ፍርድ ቤት ስሙ እንዳይሄድና ከተከሰሰም አግባብነት ባለው የህግ የበላይነት፣ ጥራቱን የጠበቀና ፍትሃዊ ውሳኔ እንዲያገኝ ማድረግ፤
ዋና ዋና ተግባራት
- ድርጅቱ ለሚዋዋላቸው ውሎችና ስምምነቶች ላይ የማማከር አገልግሎት ይሰጣል፤
 - ድርጅቱ ሲከሰስ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በማደራጀት ሙሉ መልስ ይሰጣል፤
 - ለድርጅቱ ሰራተኞችና ኃላፊዎችና የመብትና ግዴታ ምንነት እንዲረዳ ስልጠና ይሰጣል፤
 ዝርዝር ተግባራት
- የሥራ ሂደቱን ተግባራት ያቅዳል፣ያፀድቃል፣ ያደራጃል፣ ይመራል፣ ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል፤
 - ለስትራቴጂክ ዕቅድ ዝግጅት የተሟላ የክፍሉን መረጃ/ግብዓት ይሰጣል፤
 - የድርጅቱ ስራዎች በህግ አግባብ መሰረት መከናወናቸውን ያረጋግጣል’ አግባብ ካላቸው ህጎች ውጪ የሚከናወኑ ተግባራት እንዳይኖሩ ይከታተላል፤
 - ተዘጋጅተው ለውሳኔ የቀረቡ የህግ መረጃዎችን ይገመግማል፣ ከህግ አንèር ያላቸውን ጥራትና ደረጃ ይፈትሻል፤
 - ድርጅቱ የሚቀርèቸው ፖሊሲዎች፣ ውስጠ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ አሰራሮች፣ ማኑዋሉችና ሌሎች ሰነዶች አግባብ ካላቸው ህጎች ጋር የተጣጣሙ መሆኑንና ከህግ አንፃር የሚያስከትሏቸውን እንድምታዎች ይገመግማል፣ ይፈትሻል፣ ይተቻል፣ ተገቢ የማሻሻያ ሀሳቦችን ያቀርባል፤
 - የድርጅቱን ንብረቶች የኢንሹራንስ ዋስትና ከህግ አንፃር ይመረምራል
 - ከስሩ ያለው ሰራተኛ በየዕለተለት ሥራ ላይ መሆኑን ይቆጣጠራል፣ ሪፖርት ያደርጋል፤
 - በውጭም ሆነ በውስጥ በሚቀርቡ የምርመራ ሪፖርቶች ላይ የተሰጡ የማሻሻያ ሀሳቦችና የአሠራር ድክመቶች ከህግ አንፃር ከሚያስከትሉት ውጤት አንፃር በወቅቱ እንዲታረሙ ያደርጋል፣ ይከታተላል፤
 - አዋጆች፣ የድርጅቱ ደንቦች እና መመሪያዎች አፈèçም ይከታተላል’ ያረጋግጣል፤
 - በህግ ነክ ጉዳዮች ዙሪያ የድርጅቱን የሥራ አመራር ቦርድና ሥራ አመራር ያማክራል፤
 - ለስራ አመራር ቦርድና ለማኔጅመንት በቀረቡ ህግ ነክ ሪፖርቶች ላይ በሚሰጠው ውሳኔ መሰረት የእርምት እርምጃዎች መወሰዳቸውን ያረጋግጣል፣ ይከታተላል፤
 - ወቅታዊና ህጋዊ እርምጃ ባልተወሰደባቸው ጉዳዮች ላይ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ሃሳብ ያቀርባል’ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
 - የህግ ድጋፍና ምክር ለሚጠይቁ ደንበኞች አስፈላጊውን ድጋፍ እና የስራ ትብብር ያደርጋል፤
 - በፍርድ ቤቶች የሚወሰኑ’ ለትምህርትነት የሚያስፈልጉና በድርጅቱ ውስጥ ሊታወቁ የሚገቡ ጉዳዮችሲኖሩ የሚመለከታቸው የሥራ መሪዎችና ባለሙያዎች እንዲያዩዋቸው ያደርጋል፤
 - የስራ ሂደቱ የስራ ክንውን በተያዘው በጀት መሰረት መሆኑን ይከታተላል’ ያረጋግጣል፤
 - የሚዘጋጁ ክሶች’ መልሶች’ የመልስ መልሶችና ቃለ መሃላዎች ፍ/ቤት ከመቅረባቸው በፊት አግባብነት ያለው ህግ በሚያዘው መሰረት መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
 - ድርጅቱ በከሳሽነት ወይም በተከሳሽነት በሚቀርብበት ጊዜ ድርጅቱን በመወከል ተገቢ መግለጫዎችን ያዘጋጃል፣ ይከራከራል፤
 - አከራካሪ ጉዳዮችን በመከታተል ያስፈጽማል፣ ለዋና ሥራ አስፈጻሚ ሪፖርት ያቀርባል፤
 - የድርጅቱን ህግ ነክ ጉዳዮች በመመርመር፣ በመከታተልና በማጥናት ተደጋግመው የሚከሰቱ ህግ ነክ ችግሮች መንስኤዎችን ያጠናል፣ ችግሮች ከመከሰታቸው አስቀድሞ መከላከል የሚቻልባቸውን ዘዴዎች አጥንቶ ለውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፣ ተፈèሚነታቸውንና ውጤታማነታቸውን ይገመግማል ይከታተላል፤
 - በተደጋጋሚ ሥራ ላይ የሚውሉትን የድርጅቱ ህግ ነክ ሰነዶች ለይቶ በማጥናት እንደየጉዳዩ አግባብ ሊከለሱ (customize) የሚችሉ ስታንዳርድ ሰነዶችን አዘጋጅቶ ለሥራ ዝግጁ ያደርጋል፤
 - በስራ ላይ ያሉና በየጊዜው የሚወጡ ህጎችና ደንቦች በትክክል ስራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል’ ለዋና ሥራ አስፈጻሚ ሪፖርት ያቀርባል፤
 - የድርጅቱ ህግ ነክ ጽሁፎች’ ስምምነቶች’ ክሶች’ የፍርድ ውሳኔዎች የተሰጠባቸውን ሰነዶች’ ማስታወቅያዎችንና ሌሎች ህግነክ ሰነዶች በጥንቃቄ እንዲደራጁና እንዲያዙ ያደርጋል፤
 - ይግባኝ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ የይግባኝ ጊዜ ከማለፉ በፊት የይግባኝ ክስ መብቱ ለሚፈቅድለት ፍ/ቤት እንዲቀርብ ያደርጋል፤
 - ክርክር በእርቅ እንዲዘጋ አስፈላጊ ሲሆን ከከሳሾቹ ወይም ከተከሳሾቹ ጋር በመነጋገር እና በመወያየት ውጤቱን ለዋና ሥራ አስፈጻሚ ሪፖርት ያደርጋል፤
 - ድርጅቱ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር የሚያደርጋቸውን የግዥ’ የሽያጭና የመሳሰሉት ውሎችና ስምምነቶች ከህግ’ ከአዋጆች’ ከደንብና መመሪዎች አንፃር በመገምገም የህግ ድጋፍ ያላቸው እና የድርጅቱን ጥቅም የሚያስከብሩ ስለመሆናቸው/ ስለአለመሆናቸው አስተያየት ይሰጣል’ ያማክራል፤
 - የፍርድ ባለእዳዎችን ንብረት ያጣራM’ ßታ}LM፤
 - የባለእዳዎች ንብረት በፍ/ቤት እንዲያዝና እንዲከበር ያደርጋል፤
 - በክስ ምክንያት ለሚመጡ ወጪዎች ህጋዊ ደረሰኝ በመቀበል በየጉዳዩ ስም መዝግቦ ይይዛል፤
 - ከሰራተኛ ማህበሩ ጋር በሚደረጉ ድርድሮችና የህብረት ስምምነቶች ከህግ አንፃር የተሟሉና የሁለቱንም ወገን ጥቅም የሚያስጠብቁ ስለመሆናቸው’ ስለአገላለፃቸውም ሆነ ትርጉማቸው ግልጽና በድርጅቱ ላይ የተለየ ግዴታ የማያስከትሉ መሆኑን በመመርመር ለውሳኔ የሚረዳ አስተያየት ያቀርባል፤
 - የሥራ ሂደቱ ስራዎች በተቀመጠላቸው የሰዓት ልኬት (standard time) መሠረት መከናወናቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤
 - የማሰልጠን፣ የማብቃት እና ተተኪ የማፍራት (coaching and monitoring) ስራዎችን ያከናውናል፤
 - የሥራ ሂደቱን ዕቅድ፣ በጀት፣ የተለያዩ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርቶችን ያዘጋጃል፤
 - ለሥራ ዘርፉ በተያዘው በጀት መሰረት የስራ ክንውን መደረጉን ይከታተላል’ ያረጋግጣል፤
 ከቅርብ የሥራ መሪው በሚሰጠው አጠቃላይ የሥራ መመሪያና ትዕዛዝ መሰረት የሥራ ሂደቱን ሌሎች ተዛማጅ ተግባራት ይመራል፣ ያከናውናል፡፡