Skip to content
	
	
		
	
	
	
	
	
		
			Home » Printing Technology Academy  
	
		
			
	
		
					
		
		
			በአንጋፋው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የተቋቋመው የብርሃንና ሠላም የህትመት ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በ2011 የትምህርት ዘመን ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ስልጠና ኤጀንሲ እውቅና ባገኘባቸው ፡-
- 
በህትመት ቴክኖሎጂ እና በግራፊክስ አርት
 
          በደረጃ I፣ በደረጃ II እና በደረጃ III በቀንና በማታ መርሃ-ግብር
- 
በአጫጭር ስልጠናዎች በቀንና በማታ መርሃ-ግብር
 
- 
በህትመት ቴክኖሎጂ
 
- 
በግራፊክ ዲዛይንና ኤዲቲንግ
 
- 
በደንበኛ አቀባበልና ህትመት ዋጋ ትመና እና
 
- 
በሰልጣኞች ጥያቄ መሰረት በሚመቻቹ የስልጠና መርሃ ግብሮች ስልጠና በሚሰጠው ኮሌጃችን በተደራጀ መልኩ ምዝገባ ጀምረናል፡፡
 
በተጨማሪም
- 
የህትመት ቴክኖሎጂ ኮሌጁ ለሙያ ብቃት የምዘና ማዕከል (COC) የምዘና ጣቢያ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል
 
- 
ለተለያዩ ማተሚያ ቤቶች የትብብር ስልጠና በመስጠት ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡
 
ይምጡና ኮሌጃችን ባዘጋጀው የተለያዩ የህትመት ስልጠና ዓይነቶች ሰልጥነው በህትመቱ ዘርፍ ጊዜው የሚፈልገውን በቂ እውቀትና ክህሎት ያግኙ፡፡
የምዝገባው አድራሻ፡- አዲስ አበባ አራት ኪሎ ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት ቅጥር ግቢ ውስጥ የህትመት ቴክኖሎጂ ህንጻ ሬጅስትራር ቢሮ፤ 4ኛ ፎቅ፤ ስልክ ቁጥር፡ 011-155 32 33