ድርጅታችን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡-
በጨረታ አንድ (ሎት 1) ፡- ለሁለት አመት የሚቆይ የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ የግብአት አቅርቦትና የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ፤
በጨረታ ሁለት (ሎት 2) ፡- ለሁለት አመት በሚቆይ ውል ለሰራተኞች የሚሆን የደንብ ልብስ (የስራ ልብስ) ማለትም፡- ሙሉ ቱታ ብዛት 721፣ ጋዋን ብዛት 660፣ ሸሚዝ ብዛት 186፣ ሙሉ ልብስ (ብትን ጨርቅ) ብዛት 520 ሜትር፣ ከረባት ብዛት 186፣ የቆዳ የእጅ ጓንት ብዛት 150፣ የፕላስቲክ የእጅ ጓንት ብዛት 300 እና የሹራብ የእጅ ጓንት ብዛት 150 ግዥ፣
በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡ ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲስ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 300.00 ከፍለው በመግዛት የፋይናንሺያል እና የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
ጨረታው መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰአት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የፋይናንሸያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡