የፅዳት እና የፅህፈት መሳሪያዎችን ጨረታ ማስታወቂያ . . . የጨረታ ቁጥር 018/18

ድርጅታችን ለስራ አገልግሎት የሚጠቀምባቸውን ልዩ ልዩ የፅዳት እና የፅህፈት መሳሪያዎችን ማለትም  አግራፍ (paper clip 33mm) ብዛት 300 ፓኬት፣ Rubber Band (የብር ማሰሪያ ላስቲክ) ብዛት 500 ኪ.ግ፣ የኮምፒውተር ወረቀት ብዛት 2,000 ፓኬት፣ ቀይ እስክሪቢቶ ብዛት 1,000፣ እርሳስ ብዛት 500፣ ማርከር ብዛት 5,000 እንዲሁም የፅዳት እቃዎች ማለትም ዲቶል (Detol 500ml) ብዛት 400 ቦትል፣ ዱቄት ሳሙና ባለ200 ግራም (powder soap 200gm) ብዛት 3,000 ፓኬት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲስ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 300.00 ከፍለው በመግዛት ፋይናንሺያል የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ  አለባቸው፡፡

ጨረታው መስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰአት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የፋይናንሸያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡