የብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት የህትመት ስራን በተሻለ ጥራት እና ደንበኞችን የሚያረካ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ አዳዲስ ቴክሎጂዎችን በከፍተኛ ገንዘብ ከውጪ ሀገር በማስገባት እየሰራበት መሆኑ ተገለጸ፡፡ አዲስ ያስገበውን የሽፋን መጠረዣ ( ሀርድ ከቨር ሜክንግ) ማሽን ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችል የባለሙያዎች የኦፕሬሽ ቅድመ ስልጠና እየተሰጣቸውም ነው ተብሏል፡፡
በመደበኛ ህትመት የማተምና
ማጠናቀቅ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ላቀ በእውቀቱ እንደገለጹት፤ ማሽኑ የሀርድ ከቨር የማምረት ሥራውን ቀላልና ቀልጣፋ ከማድረጉም በላይ የምርቱ ጥራት በተፈለገውና ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ እንዲመረት ያስችላ ብለዋል፡፡ ማሽኑን ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችል የኦፕሬተሮች ስልጠና ከ6 በላይ ለሚሆኑ የድርጅቱ ባለሙያዎች እየተሰጠ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል፡፡ የሀርድ ከቬር ማሽኑ የሰው ሀይልን የሚቆጥብ፣ ጥራትንና የግብዓት ብክነትን በእጅጉ ይቀንሳል ያሉት አቶ ላቀው ከዚህ በፊት በሥራ መደራረብ ምክንያት የሚጓተተውን ሥራ በአጭር ጊዜ ውስጥ እዲመረት በማድረግ የድርጅቱ ገቢ እንዲያድግ ያደርጋል፤ትርፋማነትንም ይጨማራል ብለዋል፡፡ ድርጅቱ በገበያ ውስጥ ያለውን ተወዳዳሪነቱን ይጨምራል ያሉት አቶ ላቀው ደንበኛው በሚያገኘው አገልግሎት ደስተኛ ሆኖ ድርጅቱን መርጦ እንዲጠቀምበት እድል ይፈጥርለታልም ብለዋል በመግለጫቸው፡፡
ድርጅቱ ጊዜው የሚያመጣውን አዳዲስ የህትመት ቴክኖሎጂዎችን በአቅሙ ወደ ስራ በማስገባት ሂደት ላይ መሆኑ እንዳለ ሁኖ አሁን የገባው እና ወደ ስራ እንዲገባ በዝግጅት ላይ ያለው የሀርድ ከቨር ሜክንግ ከዚህ በፊት በድርጅቱ ያልነበረ እና በዓይነቱ ልዩ እንደሆነም ታውቋለ፡፡ ማሽኑ በሙሉ አቅሙ ከተሰራበት በቀን ከ4-8 ሺህ የሚደርስ የወሰኝ ኩነት የክር መዝገብ ሽፋን እና ሌሎችንም የሀርድ ከቬር ሥራዎችን ይሰራል ተብሏል፡፡ አስተባባሪው አያይዘውም፤ በዚህ ረገድ የነበረው ውዝፍ ሥራዎች ሲኖሩ ይደረግ የነበረው የዘመቻ ስራዎች ወደ ሌላ ሥራ እንዲዞር ተደርጎ አጠቃላይ የድርጅቱ እምርታዊ ለውጥ እንዲያድግ የሚያስችል ወሳኝ ማሽን ነው ብለዋል፡፡
ማሽኑን የሚመለከት የቴክኒክ ጉዳዮች በተደራጀ መልኩ እንድሰራ የኤሌክትሪክ እና የጥገና ባለሙያዎችም ከዚህ በፊት ስልጠና መውሰዳቸው ተጠቁሟል፡፡ የኦፕሬሽን ስልጠና እየወሰዱ ያሉ ባለሙያዎችም ሊያሰራ የሚያስችል መሰረታዊ እውቀት ማግኘት የሚያስችላቸውን በውጪ ሀገር ዜጎች (ቻይናዊያን) የኦፕሬተርነት ስልጠና ማግኘታቸው ሥራውን ሊያሰራቸው እንደሚያስችልም ተጠቁሟል፡፡
ድርጅቱ በገበያ ውስጥ ያለውን ተወዳዳሪነት በአግባቡ ሊያሸጋግር የሚያስችል ኋላ ቀር አሳራሮችን በማስቀረትና አዳዲስ ማሽኖችን በማስገባትና በማደራጀት፤ የሠራተኛውን አቅም በማጎልበት እና በሰራተኛው ላይ ኢንቨስት በማድረግ፤ ስትራቴጂካዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት ውጤታማ በሆኑ ወሳኝ የህትመት ዘርፍ ላይ ሙሉ አቅሙን በማሳረፍ ብሎም የደንበኞችን እርካታ እውን በማድረግ የሚጠበቅበትን ሀገራዊ አደራ መወጣት የሚያስችል አቅም እንዳለው ጠቁመዋል፡፡