ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ለተጠየቀው ሀገራዊ ጥሪ ፈጣን ምላሽ በመስጠት  ለተጎዱና ለተፈናቀሉ ዜጎች አጋርነቱን አሳየ

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ለተጠየቀው ሀገራዊ ጥሪ ፈጣን ምላሽ በመስጠት  ለተጎዱና ለተፈናቀሉ ዜጎች አጋርነቱን አሳየ

ደርጅቱ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ተከስቶ በነበረው የተፈጥሮና ሰው ሰራሸ አደጋ ምክንያት የተጎዱና ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም የሚውል ብር 1,000,000 ድጋፍ አደርጓል፡፡

ድርጅቱ በዋናነት ከሚያከናውነው የህትመት ሥራ ዘርፍ በተጓዳኝ ድርጅቱ የሚገኝበትን አካባቢ ማህበረሰብ እና በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ የማህበራዊ ኃላፊነትን ሥራ በዕቅድ አካቶ እያከናወነ እንደሚገኝ የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነትና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ኃይለ ገልፀዋል፡፡

እንደ አቶ ዳንኤል ገለፃ፤ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት  የማህበራዊ ኃላፊነት ሥራዎቹን የሚያከናውንባቸው ወይም የሚቀርቡለትን የድጋፍ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጥበት የራሱ የሆነ መርሃ-ግብርና የአሰራር ስርዓት እንዳለውና በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች  ለሚገኙ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የተደረገው የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ የድርጅቱን ለሀገራዊ ጥሪዎች የሚሰጠውን ምላሽና ለዜጎች ያለውን ወገናዊነት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

በቀረበው ሀገራዊ ጥሪ ተሳትፎ ያደረጉ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ለማመስገን ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ.ም በተዘጋጀው መርሃ-ግብር የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ ታገሰ ጫፎ ተገኝተው ለሀገራዊ ጥሪው ፈጣን ምላሽ ለሰጡ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የምስጋና የምስክር ወረቀት አበርክተዋል፡፡