ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ በተዘጋጁ ሁለት አውደ ርዕዩች ላይ ተሳትፎ አደረገ

በተሳትፎው አንጋፋው ድርጅት በሀገራችን ኪነጥበብ  ዘርፍ ያለውን ሚና ያስቃኘ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ከየካቲት 15 እስከ 18 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መፃህፍት አገልግሎት እና በአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ በግዮን ሆቴልና በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መፃህፍት አገልግሎት ዋና መ/ቤት ቅጥር ግቢ በተገነባው ባለ አስራ ሶስት ወለል አዲስ ህንፃ ላይ በተዘጁ አውደ ርዕዮች ላይ በመሳተፍ ምርትና አገልግሎት ማስተዋወቅ እንዲሁም የህትመት ውጤቶችን ሽያጭ ማከናወን የተቻለ ሲሆን በአስር ሺዎች በሚገመቱ ጎብኚዎች  ተጎብኝቷል፡፡ በቆይታው በአውደ ርዕዮቹ ላይ ለነበረው ተሳትፎ የምስክር ወረቀት ያገኘ ሲሆን በአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ባዘጋጀው  በአውደ ርዕይ ላይ  በተሳተፉ ተቋማት መካከል በነበረው ውድድር የሶስተኛ ደረጃን በመያዝ የእውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል፡፡