ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡
ቀኑ በድርጅቱ ሲከበር የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽታሁን ዋለ የማኔጅመንት አባላትና ከየስራ ክፍሉ የተውጣጡ ሰራተኞች በበዓሉ ላይ ታድመዋል፡፡
የሰንደቅ ዓላማ መስቀል ስነ-ስርዓቱን የፌዴራል ፖሊስ አባላት በወታደራዊ ሰልፍ ያደመቁት ሲሆን የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽታሁን ዋለ ሰንደቅ ዓላማውን በመስቀል ቀኑን አክብረዋል፡፡