አረንጓዴ አሻራ

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በሀገር አቀፍ ደረጃ የቀረበውን የአረንጓዴ አሻራ ቀን አስመልክቶ አራዳ ከ/ከተማ ወረዳ 9 ጤና ጣቢያ ልዩ ስሙ ባሻ ወልዴ ችሎት ኮንዶሚኒየም አካባቢ ችግኞችን ተከለ፡፡

በኢፊዲሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ በቀረበ ጥሪ ሐምሌ 22 በተደረገው ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ቀን የችግኝ ተከላ   ተሳታፊ የሆነው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ቀደም ሲል ሰኔ 30/2011 ዓ.ም ለ16ኛ ጊዜ በድሬ ግድብ እና በባሻ ወልዴ ችሎት አካባቢ ከ3000 በላይ ችግኞችን መትከል ችሏል፡፡