ከሐምሌ 7-20/2011 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) አዘጋጅነት በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ሁለገብ ስታዲየም በተዘጋጀው የክረምት ስፖርታዊ ውድድር ላይ ታሳተፊ የነበረው ብርሃንና ሰላም ውጤት ቀንቶታል ተባለ፡፡
በ
ዘጠኝ የስፖርት ዓይነቶች ለመወዳደር ወደ ስፍራው ያቀናው የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የስፖርት ልዑካን ቡድን በነበረው ቆይታ በተለያዩ የውድድር ዓይነቶች የተሻለ ውጤት ያስመዘገበ ሲሆን በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ሁለገብ ስታዲየም በተዘጋጀው የክረምት የስፖርት ውድድሮች በርካታ ዋንጫዎችንና የምስክር ወረቀቶችን አስገኝቷል፡፡ ድርጅቱ በተወዳደረባቸው የስፖርት ዓይነቶች ሜዳሊያዎችን ጨምሮ የለተያዩ ሽልማቶችን ያገኘ መሆኑም ታውቋል፡፡ በገበጣ እና በጠረጴዛ ወንዶች ቴኒስ ስፖርቶች የዋንጫ ተሸላሚ የሆነው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በበጋ ወራት የስፖርት ውድድሮች በከረንቡላና በገበጣ ሁለት ዋንጫዎች ባጠቃላይ በበጋና በአገር አቀፈፍ ውድድሮች ላይ አራት ዋንጫዎችና ሌሎች ሜዳሊያዎች የተገኘበት እና ለስፖርታዊ ውድድር መሳካት ላደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍ በኢሰማኮ በኩል የምስጋና እና የእውቅና ሽልማት ተበርክቶለታልም ተብሏል፡፡
የገበጣ ስፖርት አሸናፊው የስፖርት ልዑክ አቶ ግዛቸው ይልማ ከተደረገው ውድድርና ከተገኘው ውጤት ባሻገር ከሌሎች ተቋማት ከመጡ ተወዳዳሪ ሰራተኞች ጋር የልምድ ልውውጥና የወንድማማችነት ስሜትን መፍጠር የተቻለ መሆኑን ገልፀው በቀጣይ ለሚደረጉ ውድድሮች የተሻለ ውጤት ለማሰመዝገብና የድርጅቱን ስም ማስጠራት እንዲቻል በየደረጃው ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
አቶ ሽታሁን ዋለ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ (ተወካይ) በውድድሩ ማጠናቀቂያ ፕሮግራም ዕለት ተገኝተው ተወዳዳሪ ስፖርተኞችን ያበረታቱ ሲሆን ስፖርቱ የተሻለ እንቅስቀሴ እንዲያሳይ ድርጅቱ አስፈላጊ ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡ ስፖርተኞቹ በቆይታቸው ላሳዩታል ስፖርታዊ ጫዋነት አድንቀው ድርጅቱን ማስተዋወቅ መቻላቸውን እና ጠቁመው በቀጣይ እንደዚህ ዓይነት ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንደለበት አስገንዝበዋል፡፡ የሠራተኛ ማህበር ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ተስፋለም ሀይሉ በበኩላቸው፤ ስፖርተኞቹ በቆይታቸው ምንም ዓይነት ክፍተት ሳይፈጠር፤ተልዕኳቸውን በተሳካ መልኩ መወጣት መቻላቸውን አድንቀው ስፖርቱን የተሻለ እንዲሆን በቀጣይ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ ሽታሁን ዋለ የተገኙ ዋንጫዎችን ከስፖርተኞች እጅ ተቀብለዋል፡፡