ድርጅቱ ብሔራዊ ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ በህትመት፣ ድልድል፣ ስርጭትና ሌሎች ተጓዳኝ ሥራዎች ላይ ለነበረው ከፍተኛ አስተዋፅኦ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል፡፡

ነሐሴ 25 ቀን 2016ዓ.ም በትምርት ሚኒስቴር በተዘጋጀው 33ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ላይ በአገር አቀፍ ፈተና ስኬታማ ሥራዎች ላከናወኑ የፌደራልና የክልል ባለድርሻዎች ዕውቅና በተሰጠበት መድረክ ላይ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት አንዱ በመሆን የእውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል፡፡ የምስክር ወረቀቱን የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሽታሁን ዋለ በአክብሮት አበርክተዋል፡፡
በ2016ዓ.ም በድርጅቱ የታተመውን የሃገር አቀፍ ፈተና ከመቼውም ጊዜ በተሻለና ያለ አንዳች እንከን በመከናመኑ በድርጅት ደረጃ ለዚህ ሥራ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለነበራቸው የድርጅቱ አመራርና ሰራተኞች የምስጋናና የእውቅና መርሃ ግብር መካሄዱ ይታወሳል፡፡