ሥልጠናው ሠራተኞች በሥራ ላይ ሊኖሯቸው የሚገባ ስነ-ምግባርንና የሙስና ወንጀል ከመፈፀሙ በፊት ሂደቱን ማምከን የሚያስችል የተቀናጀ ሥራ መሥራት የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ከመጋቢት 26/2014 ዓ.ም እስከ መጋቢት 30/2014 ዓ.ም በተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ከተለያየ የሥራ ክፍሎች የተውጣጡ ከሁለት መቶ በላይ የድርጅቱ ሠራተኞች ተሳትፈዋል፡፡
ስልጠናው ሠራተኞች በሥራ ላይ ሊኖሯቸው የሚገባ የስራ ስነ-ምግባርንና የሙስና ወንጀል ከመፈፀሙ በፊት ሂደቱን ማምከን የሚያስችል የተቀናጀ ሥራ መሥራት የሚያስችል ግንዛቤ መፍጠርን ዓላማው ያደረገ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በስልጠናው ከስራ ሥነ-ምግባር ምንነት ጀምሮ የተሟላ ሥብዕና ፤ የስራ ሥነ-ምግባር መርሆች፤ የተሟላ ሥብዕና፤ውጤታማነት /ሙያዊ አቅም/ እና የቡድን ስራ ሌሎች ተያያዥ ፅንሰ ሀሳቦች በአቶ ተካልኝ ደመቀ ተሰጥተዋል፡፡ በተያያዘም የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ምንነት፤ አስፈላጊነት እና ዓላማ፤ የአስቸኳይ የሙስና መከላከል ሥራ የህግ ማእቀፎች እና መርሆዎች አንዲሁም በአስቸኳይ ሙስና መከላከል ሥራ ላይ በስነ ምግባር መከታተያ ክፍሉ የሚከናወኑ ተግባራት ያተኮረው የስልጠናው ክፍል በወ/ሮ ሉሊት ጌታቸው ተሰጥቷል፡፡
እንደ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክተር ገለፃ የስነ-ምግባርና ሙስናን የመከላከል ሥራ ለአንድ የሥራ ክፍል የሚተው ባለመሆኑ የድርጅቱ አመራርና ሰራተኞች በሚመቻቹ የስልጠና እድሎች በመጠቀም ግንዛቤያቸውን አሳድገው በተቀናጀ መልኩ ሙስናን በመከላለል የድርጅቱን ስኬታማነት ሊያረጋግጡ ይገባል ብለዋል፡፡
ስልጠና በሁለተኛ ዙር ለተቀሩት ሰራተኞች ለመስጠት መታቀዱን ከአቶ መለሰ በቀለ የድርጅቱ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክተር መረዳት ተችሏል፡፡