የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ሥራ አመራር ቦርድ፣ ማኔጅመንትና መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር የድርጅቱን የ2012 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ በጋራ ገመገሙ፡፡

የሁለተኛውን የድርጅቱን ስትራቴጂክ ዕቅድን መነሻ በማድረግ የተዘጋጀውና በየደረጃው ተገምግሞ ማሻሻያዎች የተደረጉለት የ2012 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ግንቦት 17/2012 ዓ.ም ጊዮን ሆቴል በነበረው የዕቅድ ግምገማ መድረክ የድርጅቱ ሥራ አመራር ቦርድ ሰባሳቢ አቶ ወርቁ ጓንጉልን ጨምሮ የሥራ አመራር ቦርድ አባባላት፤ የማኔጅመንት አባላትና የመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር አመራር አባላት በተገኙበት ተገምግሟል፡፡

መሪ ዕቅዱ ያለፈውን 2ኛ የዕድገትና ትራንፎሜሽን የ3 ዓመታት የድርጅቱ ዕቅድ እና አፈጻጸም መነሻ ያደረገ ሲሆን በአፈጻጸም ወቅት የታዩ ጠንራና ደካማ አሰራሮች በአጭሩ ተካተዋል፡፡ በመድረኩ የድርጅቱ የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መኮንን አበራ  መሪ ዕቅዱን ያቀረቡ ሲሆን ያለፉትን 3 ዓመታት መነሻ በማድረግ ከድርጅቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣም ሆኖ የ2012 በዓ.ም መሪ ዕቅድ ተግምሟል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙ ተሳፊዎችም በተዘጋጀው ዕቅድ ላይ  አስተያየት እና የተለያዩ ሀሳቦችን አንስተው ውይይት አድርጎባቸዋል፡፡ የበጀት ዓመቱ ምርት፣ የሽያጭ እና የትርፍ የድርጅቱን ግብ መምታት በሚያስችል መልኩ  የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ታሳቢ እንዲደረጉ እና ለሥራው የሚያስፈልጉ የስራ ማስኬጃ እና የካፒታል በጀት ፍላጎት የተካተተበት ሲሆን መሪ ዕቅዱ  ወደ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ተልኮ ተግምግሞ ከፀደቀ በኋላ ተግባራዊ እንሚደረግ መረዳት ተችሏል፡፡