የእሳት አደጋ መከላለልና መቆጣጠር ስልጠናው ከሰኔ 17-21/2011 ዓ.ም ለተከታታይ አምስት ቀናት ከአዲስ አበባ ከታማ አስተዳደር የእሳት ድን
ገተኛ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን ማሰልጠኛ ኢንስትቲዩት በመጡ አሰልጣኞች ተሰጠ፡፡ በሥልጠናው ከየሥራ ክፍሉ የተውጣጡ ሃያ ሰባት ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን የእሳት አደጋን ለመከላከል የሚያስችል ብሎም በጅምር ያለ እሳትን ለማጥፋት የሚያስችሉ የንድፈ ሀሳብና የተግባር ልምምድን የተከታተሉበት እንደነበር የድርጅቱ የሴፍቲ ባለሙያ አቶ ጌታው ይርጋ ገልፀዋል፡፡
እንደ አቶ ጌታው ገለፃ በስልጠናው ሰልጣኞች በድርጅቱ እሳትን ለመፍጠር ምቹ የሆኑ ተቀጣጣይ ነገሮች በብዛት ከመኖራቸው ጋር ተያይዞ ለራተኞችን በጅምር ያለ እሳትን ለማጥፋት የሚያስችል ስልጠናን በመስጠት የቅድመ ጥንቃቄው ሥራ መስራቱ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ እንደሆነና ሥልጠናውን የተካፈሉ የድርጅቱ ሰራተኞች በንድፈ ሀሳብና በተግባር ያገኙትን ሥልጠና ለራሳቸውም በመጠቀም ለሌሎች ሰራተኞች ግንዛቤ በመፍጠር አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡