የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ሰራተኞች የደም ልገሳ መርሃ- ግብር አካሄዱ

የድርጅቱ ሰራተኞች በፈቃደኝነት ደም እንዲለግሱ በቀረበው ጥሪ መሰረት ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች የተውጣጡ አስር ሰራተኞች ህዳር 11/2012ዓ.ም በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ዋና መስሪያ ቤት በሚገኘው ደም ባንክ ማዕከል በመገኘት ደም ለግሰዋል፡፡

የተለያዩ አደጋዎች እና ህመም አጋጥሟቸው ህክምና ሲደረግላቸው ደም የሚያስፈልጋቸው ወገኖችን ህይወት ለመታደግ ደም መለገስ እጅግ የተከበረ ሰብዓዊ ተግባር እንደሆነ የገለፁት የደም ልገሳ መርሃ-ግብሩ ተሳታፊዎች በእንደዚህ ያሉ በጎ ተግባር ላይ በመሳተፍ  ለራሳቸው የህሊና እርካታ ከማግኘት ባሻገር የድርጅቱንም ገፅታ መገንባት እነደሚቻል ጠቁመዋል፡፡

ፈቀደኛ ደም ለጋሽ ሰራተኞቹ ከዚህ ቀደም በተለያየ አጋጠሚ እና ቦታ ደም ለግሰው እንደሚያውቁ ገልፀው በተደራጀና ሌሎችንም ፈቃደኛ ደም ለጋሽ የድርጅቱ ሰራተኞች ባሳተፈ መልኩ የደም መለገስ መርሃ-ግብሩ ቀጣይነት ቢኖረው የሚል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ በተያያዘም በድርጅቱ የደም ለጋሾች ማህበር ቢቋቋም የሚሉ አስተያየቶች ደም ከለገሱ ሰራተኞች የተነሳ ሲሆን ሀሳቡም ቡሁሉም ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘ ሃሳብ ነበር፡፡