ውይይቱ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ያተኮረውና ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ ግንዛቤ የሚፈጥር ከመሆኑም በላይ የድርጅቱ ሰራተኞች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ሀሳቦች እንዲያንፀባርቁ ያስቻለ ነበር፡፡
ጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደው ውይይት ላይ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሽታሁን ዋለን ጨምሮ ም/ዋና ሥራ አሰፈፃሚዎች፤ የማኔጅመንት አባላትና አጠቃላይ ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ ህዝብ ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር ተጀምሯል፡፡
በዕለቱ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሽታሁን ዋለ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት አመራርና ሰራተኞች የውይይቱን ዓላማና ግቦች በማስገንዘብ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳባቸውን በነፃነት አንስተው መወያየትና ጠንካራና የበለፀገች ሀገር በመገንባት ሂደት ላይ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ጠቁመው፡፡
ለአንድ ቀን በዘለቀው የውይይት መርሃ ግብር ለውይይት መነሻ እንዲሆን “ሀብት የመፍጠር ጉዟችን ያጋጠመው ተግዳሮቶች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ በድርጅቱ ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ (ሀብት አመራር ዘርፍ) አቶ መለሰ ስሜነህ ቀርቦ ተሳታፊዎች በተነሳው ርዕሰ ጉዳዮችና አጠቃላይ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ያሏቸውን ጥያቄና አስተያየት እንዲያነሱ በተሰጠው እድል መሰረት የተለያዩ ሀሳቦች ተነስተዋል፡፡
በውይይቱ ማጠቃለያ ከቀረበው ሰነድ በተጨማሪ በተሳታፊዎች ገንቢ የሆኑ አስተያየቶች እንደቀረቡ የገለፁት የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በተጨማሪም ሀሳቦቹ ተጠናቅረው ወደሚመለከተው የመንግስት አካል የመላክ ስራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡