በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 14ኛ ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል ተከበረ

 ጥቅምት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30  ለ14ኛ ጊዜ በመላው ኢትዮጵያ በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ ሉዓላዊነት ለሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ በሚል መሪ ሃሳብ የሰንደቅ ዓላማ ቀን የተከበረ ሲሆን በተመሳሳይ የድርጅቱ  ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሽታሁን ዋለን ጨምሮ የማኔጅመንት አባላት፣ የመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር አመራሮች፣ ሰራተኞች እና የፌደራል ፖሊስ አባላት በተገኙበት ሰንድቅ ዓላማ በመስቀልና የኢትዮጵያን ሕዝብ ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር  በዓሉ ተከብሯል፡፡